Tender Detail

Tender Details


በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሀራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


 

የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

የሀራጅ ጨረታ ቁጥር 043/2017

 

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሀራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት:-

በሀራጅ ጨረታ ቁጥር 043/17 በ13/09/2017 የተለያዩ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ጫማዎች፣ ስፔርፓርቶች፣ የሞባይል ቀፎዎች፣ ጎማዎች፣ ኮስሞቲክሶች ፣የንጽህና መጠበቂያዎች ፤ መነጽሮች ፣ የእጅ ሰዓቶች ፣ የመሬት ምንጣፎች ኤጋ የቤት ክዳን ቆርቆሮዎች ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች

  1. በዘርፋ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑ ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ እና መለያ ቁጥሩን ማቅረብ የሚችል መሆኑን ይጠበቅበታል፡፡
  2. ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች የሚገኙት በድረዳዋ ሙድአነኖ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የውርስ ዕቃ መጋዘን ውስጥ ነው።
  3. በሀራጅ ጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተጠቀሰው ቀን መሰረት ድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ገቢ አሰባሰብ እና ዋስትና አያያዝ ቡድን ገንዘብ ያዥ ቢሮ በመቅረብ ብር 100 በመክፈል ሪሲት በመውሰድ ዘወትር በስራ ሰአት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 1:30 እስከ ቀኑ 12፡00 ሰአት እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡00 ሰአት እስከ ቀኑ 6፡00 ዕለት ንብረቱ በሚገኝበት መጋዘን በመቅረብ ማየት ይቻላል፣ ነገር ግን እቃዎቹን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር የቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።
  4. ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ በድሬዳዋ ሙድአነኖ ግቢ ነው።
  5. ለሀራጅ ጨረታ ለሽያጭ የቀረቡት እቃዎች በኮድ የተከፋፈለ ሲሆን ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን አለበት፡፡
  6. ተጫራች በሀራጅ ጨረታ ለመጫረት ዕቃዎች ለመግዛት ለሚያቀርበው ዋጋ 5% ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ (CPO) በባንክ (ንግድ ባንክ) የተረጋገጠ በድሬዳዋ ጉምሩከ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል፡
  7. በሀራጅ ጨረታ ለመጡት ለእያንዳንዱ ኮዶች በጨረታ ዋስትና ማስከበረያ (CPO የዕቃውን ዋጋ 5% ብር በባንክ (ንግድ ባንክ) የተረጋገጠ በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. የሀራጅ ጨረታ ለሚካሄደው በማስታወቂያ መሰረት በእለቱ ጠዋት በ2:00 ሰዓት ምዝገባ ጀምረን እንደተጠናቀቀ በ4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ጨረታው ይጀምራል።
  9. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች በጨረታ ዋስትና ያስያዘው ሲፒኦ ከሚከፍለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን በተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ ሲፒኦ በሶስት የስራ ቀናቶች ውስጥ ተመሳሽ ይደረግላቸዋል፡፡
  10. አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደረበትን እቃዎች አሸናፊ ስለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበት ገንዘብ ገቢ በማድግ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል፡፡
  11. ከላይ በተራ ቁጥር 10 ላይ በተገለጸው ቀናቶች ውስጥ ክፍያውን ፈጽሞ ዕቃውን ያልተረከበ በተጫራች ለጨረታ ማስከበረያ ያስያዘውን ሲፒኦ ለባለስልጣኑ መ/ቤት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል፡፡
  12. የጉምሩክ ኮምሽን ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራረያ በስልክ ቁጥር 0915460970 (0912885746) መደወል ይቻላል፡፡

 

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender