Tender Detail

Tender Details


የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተገለፁትን ለክረምት የፋብሪካ ጥገና የሚያስፈልጉ መለዋወጫዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Metehara Sugar Factory (መተሐራ ስኳር ፋብሪካ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር MSF/LP/02/2025

 

የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተገለፁትን ለክረምት የፋብሪካ ጥገና የሚያስፈልጉ መለዋወጫዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ጥቅል አንድ - የኤሌክትሪክ እቃዎች (Electrical Materials)

ጥቅል ሁለት፡- ቤሪንግ (Bearing)

ጥቅል ሶስት፡- የኤሌክትሪክ እና ኢንስትሩመንት እቃዎች (AC, Fereon gas, Compressor & others)

ጥቅል አራት፡- የተለያዩ ብረቶች (Sheet Metals, round iron, Bronze bar)

ጥቅል አምስት፡- ቤሪንግ (Bearing)

ጥቅል ስድስት:- ሲል (Oil Seal)

ጥቅል ሰባት፡- የተለያዩ መለዋወጫዎች (V-belt, hacksaw, spanner, Gasket Maker, Galvanized soaket, U-pvc pipe)

በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

  1. ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን የሀገር ውስጥ ገቢ ግብር አጠናቀው የከፈሉና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  2. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች ለእያንዳንዱ ጥቅል የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሠዓት ሜከሲኮ አደባባይ ፊሊፕስ ህንፃ ግዥ ቡድን 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 215 የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ገዝተው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሲገዙ የንግድ ፈቃድ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሠነድ ጋር የታደሰ የንግድ ፈቃድ የአቅራቢዎች የምዝገባ ሠርተፍኬት እና ለጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ከ1.5 - 2% የሚሆን በሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ (Proforma invoice) ላይ በማዘጋጀት በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ እ.ኤ.አ. ግንቦት 21 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ጧቱ 4፡00 ሠዓት ድረስ ሜክሲኮ ፊሊፕስ ሕንጻ ቢሮ ቁጥር 119 ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው በዕለቱ ግንቦት 21 ቀን 2017 ዓ.ም ከጧቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 119 ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ፡፡
  7. ፋብሪካው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ስልክ ቁጥር 0115-505607, 0115-505633

ሜክሲኮ አደባባይ ፊሊፕስ ሕንፃ አዲስ አበባ

 

የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ

 

Save Tender