Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara Water and Energy Bureau (በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የውሃ እና ኢነርጂ ቢሮ)
  • Address Bahir Dar, Ethiopia, Phone: 058-22-201-32
  • Website
  • Deadline29 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-29 00:00:00
  • Categories Energy, Power And Electricity , Electronics Materials

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የውሃ እና ኢነርጂ ቢሮ በመደበኛ በጀትና እና ከተለያዩ ፕሮጀክቶች በተገኘ በጀት ሎት 1- የሶላር እቃዎች ሎት 2 - የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ተወዳዳሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Amhara Water and Energy Bureau (በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የውሃ እና ኢነርጂ ቢሮ)


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 10/2017

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የውሃ እና ኢነርጂ ቢሮ በመደበኛ በጀትና እና ከተለያዩ ፕሮጀክቶች በተገኘ በጀት ሎት 1- የሶላር እቃዎች ሎት 2 - የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ተወዳዳሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆንም በጨረታው ለመሳተፍ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው:
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው እና የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1 እና 2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. የእቃው ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የውሃ እና ኢነርጂ ቢሮ ቁጥር 23 ማግኘት ይቻላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ /CPO / ለሚወዳደሩበት እቃ 2% ማስያዝ አለባቸው።
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በውሃ እና ኢነርጂ ቢሮ ቢሮ ቁጥር 27 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ የመቁጠሪያ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ ይቆያል።
  9. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በመሙላት ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ 16ኛው ቀን 8፡00 ሠዓት ከመድረሱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል ፤ ጨረታው በዚሁ ቀን 8፡00 ሠዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ የጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዢ ክፍል ቢሮ ቁጥር 27 8፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
  10. የጨረታ መዝጊያ ቀን /16ኛው ቀን/ በዓል ቀን ከሆነ በተመሳሳይ ሠዓት በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል። ከሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  11. ቢሮው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 058-22-201-32/058-220-10-78/ በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የውሃ እና ኢነርጂ ቢሮ

 

Save Tender