የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2017 የበጀት ዓመት ሜዲካል ኢኩፕመንት፤ የኮሚኒቲ ፋርማሲ መድኃኒቶች ራዲዮሎጂ ኢንፎርሜሽን ሲስተም (Radiology Information system RIS) እና ፒክቸር አርቺቪንግ (Picture archiving) እና ኮሙኒኬሽን ሲስተም (Communication System PACS) ፤ ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ኮፒ ማሽን፣ ኮምፒውተር፤ ዩፒኤስ (UPS)፤ ቴሌቪዥን እና ፕሪንተር ለሁለተኛ ጊዜ ለመሸጥ በግልፅ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡
Adama Hospital Medical College (የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2017 የበጀት ዓመት ሜዲካል ኢኩፕመንት፡-
- የኮሚኒቲ ፋርማሲ መድኃኒቶች ለሶስተኛ ጊዜ ለመግዛት፣
- ራዲዮሎጂ ኢንፎርሜሽን ሲስተም (Radiology Information system RIS) እና ፒክቸር አርቺቪንግ (Picture archiving) እና ኮሙኒኬሽን ሲስተም (Communication System PACS) ለሶስተኛ ጊዜ ለመግዛት
- ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ኮፒ ማሽን፣ ኮምፒውተር፤ ዩፒኤስ (UPS)፤ ቴሌቪዥን እና ፕሪንተር ለሁለተኛ ጊዜ ለመሸጥ በግልፅ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች የምታሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ትችላለችሁ፡፡
- 2017 ዓ.ም ታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ በዘርፉ ያላችሁ፣
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባችሁን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ አለባችሁ።
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃ ግዥ መ/ቤት ድረስ በራሳቸው ወጪ ማቅረብ አለባቸው፣
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ጨረታ ሰነድ ኮፒና ኦሪጅናል ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማሽግ አለባቸው፡፡
- ስርዝ ድልዝ ያለው፣ የማይታይ የጨረታ ሰነድ ወይም የዋጋ ዝርዝር ተቀባይት የለውም፡፡
- ጨረታውን ከአሸነፉ በኋላ የውል ማስከበሪያ የአሸነፉበትን ዋጋ 10% ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከኮሌጁ ግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት ክፍል ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ አለባቸው፡፡
- ሰነዱ የሚሸጠው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21/09/2017 ዓ.ም ከቀኑ 6:00 ሰዓት ብቻ ነው፡፡
- የኮሚኒቲ ፋርማሲ መድኃኒቶች ጨረታው የሚከፈተው በ21/09/2017 ዓ.ም ቀኑ 8:30 ሰዓት ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ራዲዮሎጂ ኢንፎርሜሽን ሲስተም (Radiology Information system RIS) እና ፒክቸር አርቺቪንግ (Picture archiving) እና ኮሙኒኬሸን ሲሰተም (Communication System PACS) ጨረታው የሚከፈተው በ21/09/2017 ዓ.ም ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ተጫራቾች/ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ኮፒ ማሽን፣ ኮምፒውተር ፣ ዩፒኤስ (UPS)፣ ቴሌቪዥን እና ፕሪንተር ጨረታው የሚከፈተው በ21/09/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች /ህጋዊ ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች የተጫረቱበትን ንብረት በ5 ቀናት ውስጥ ማንሳት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉትን ዋጋ በመስሪያ ቤቱ ሰነድ ብቻ ላይ መሆን አለበት፡፡
- ጨረታ ማስከበሪያ ሰሶስቱም ጨረታ ለየ ብቻ 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በ CBE, CBO እና በ Singe ባንክ ብቻ ማስያዝ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 022-8-12-39-56 ደውለው መረዳት ይችላሉ፡፡
የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ
