ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ ለ2017 በጀት ዓመት ግዥ ከዚህ በታች የተቀመጠውን ግዢ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ ለ2017 በጀት ዓመት ግዥ ከዚህ በታች የተቀመጠውን ግዢ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ
ስለሆነም፡-
- በመስኩ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
- በመስኩ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
በዚሁ መሠረት ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የወሳኝን ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ በአካል በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል እንድትገዙ፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ግዢ መጠን 2% ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋ ኤጀንሲው ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ በመሙላትና የድርጅታችሁን ማህተም በማሳረፍ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የመወዳዳሪያ ፖስታዎችን ለሎት ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሠነድ ኦርጂናልና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ መቅረብ ያለበት ሲሆን በጨረታ መክፈቻው ቀን ቴክኒካል ሠነድ ብቻ የሚከፈት ሲሆን ቴክኒካል ያለፈ ብቻ ለፋይናንሻል የሚወዳደሩ ይሆናሉ፡፡ የሚቀርበው ዋጋ ከላይ የማወዳደሪያ ሃሳብ መቅረቢያ አንቀጽና ሁኔታ ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት፡፡ በተጨማሪም አሸናፊው ተጫራች የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመንግሥት ግዢ ኤጀንሲ በሀገር ውስጥ ገበያ አነስተኛ ዋጋ ላሳዩ ግዢዎች ላወጣው ጠቅላላ የውል ሁኔታዎች መሠረት ተፈጸሚ ይሆናል። ጨረታውም በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ የጨረታው ሳጥን ታሽጎ በ8፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የበዓል ወይም የዕረፍት ቀን ከሆነ በቀጣይ በሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-
አድራሻ፡- የማ/ኢት/ክ/መግቢ ውስጥ መጥቶ በአካል ማነጋገር ይቻላል፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ
