መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የሰነድ ቁጥር 115
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ቁሳቁሶቹም ፦
- አሉሚኒየም ነክ ከሆኑ ግብአቶች የተሠሩ ያገለገሉ አልጋዎች፣ በርና መስኮቶች፣ ሼልፎች፣ ፋይል ካቢኔቶች እና ቁርጥራጭ የአሉሚኒየም ስክራፖች፣
- የተለያየ መጠን ዓይነት ያላቸው ያገለገሉ የእንጨትና የብረት ወንበሮች ያገለገሉ ጠረጴዛዎችና የተሰባበሩ ጣውላዎች ናቸው።
በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች አዲስ አበባ ከተማ ወረዳ 03 (በተለምዶ አያት ኮንዶሚኒየም ከጠበል መድኃኒአለም ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት) በሚገኘዉ በማዕከሉ ዋና መ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ቁሳቁሶች በሚገኙበት ቦታ በመገኘት ከተመለከቱ በኋላ በማዕከሉ የጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ድረስ በመምጣት ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሰነዱ በቁጥር 4 ቅጥር ግቢያችን ውስጥ ለሽያጭ የተዘጋጁትን ዝርዝር የያዘ ሲሆን እየተዘዋወሩ ከተመለከቱ በኋላ እያንዳንዱ ቁጥር አንፃር የተለዩትን ዕቃዎች የሚገዙበትን ዋጋ በመሙላት ካሸጉ በኋላ የጠቅላላ አገልግሎቱ ድረስ የጨረታውን ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ብር 160,000 (አንድ መቶ ስልሳ ሺህ ብር) ከያዘ ሲፒዮ ጋር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታዉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አስር ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ11ው ቀን ከጧቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ እለት ክል በ5፡00 ሰዓት ተጫራቾቹና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን በ11ው ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀናት ከሆነ ጨረታዉ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡ ድርጅቱ የተሻለ እድል ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0930796413 ወይም 0975264159 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር
