ድርጅታችን ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት Horizontal Web Offset Press Machine (Reconditioned) 4 unit ብዛት 1 በድጋሚ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Berhanena selam printing enterprise (ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት)
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን Horizontal Web Offset Press Machine (Reconditioned) 4 unit ብዛት 1 በድጋሚ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅቱ አዲስ ህንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመስስ ብር 300.00 ከፍለው በመግዛት የፋይናንሺያል እና የቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውን እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ ነባሩ ህንፃ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፡፡
ጨረታው 19/9/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ (ከላይ የተገለፁ ለቅድመ ገምገማ የሚያገለግሉ ዶክመንቶች፣ የጨረታ ማስከበሪያ) ብቻ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ነባሩ ህንፃ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡ የፋይናንሽያል የመጫረቻ ሠነዶች የሚከፈቱት ቴክኒካል ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው፡፡ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት
ስልክ ቁጥር 011-1-55-52-30
ድረ ገፅ (www.ethbspe.org)
Berhanena selam printing enterprise
አዲስ አበባ
