Tender Detail

Tender Details

  • Company በዋግ ኽምራ ዞን የሠቆጣ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
  • Address አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0334400416
  • Website
  • Deadline30 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-30 00:00:00
  • Categories Construction and Water Works , Building Construction

በአማራ ብሄራዊ ከልላዊ መንግስት በዋግ ኸምራ ዞን የሠቆጣ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለወረዳው በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለጸውን ከተራ ቁጥር 1 እስከ ተራ ቀጥር 2 ድረስ ያሉ ግንባታዎች በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳደሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡

በዋግ ኽምራ ዞን የሠቆጣ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት


 

ብሄራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሄራዊ ከልላዊ መንግስት በዋግ ኸምራ ዞን የሠቆጣ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለወረዳው በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለጸውን ከተራ ቁጥር 1 እስከ ተራ ቀጥር 2 ድረስ ያሉ ግንባታዎች በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳደሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም

    • የተለያዩ የውሃ ግንባታዎች ሁሉንም ደረጃ ያለው
    • ባለ 4 ወለል ህንጻ ግንባታ ደረጃ 4 እና ከዚያ በላይ ያለው መሳተፍ ይችላል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የ2017 ዓ/ም ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረበ የሚችሉ።
  2. ግብር ከፋይነት መለያ ቀጥር /TIN/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. የግዥ መጠናቸው ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ተጫራቾች ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቀጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን 1 ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  5. የግንባታው አይነትና ዝርዝር መገለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች በተራ ቀጥር 1 የውሃ ግንባታ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለሰ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ በተራ ቁጥር -2 ለተገለጹት የህንጻ ግንባታ ለአንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከገንዘብ ቤት መግዛት ይችላሉ።
  7. የግንባታው ጨረታ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ21 ሃያ አንድ (ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይቆያል።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የግንባታ ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክበተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ወይም በሰቆጣ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በመ/ሂ-1 ገቢ አድርጎ ኮፒውን ከዋናው የጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
  9. ማንኛውም ተጫራቾች የውሃ ግንባታ የጨረታ ሀሳቡን በአንድ በታሸገ ፖስታ የህንጻ ግንባታ ፋይናንሻሉን እና ቴክኒካል መረጃዎች በተለያየ ፖስታ በማሸግ በግዥ/ን/አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከ 01/09/2017 እስከ 21/09/2017 ዓ/ም ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በተጨማሪም በጨረታ ሰነዱ ላይ ስማቸው፣ ፊርማቸውን ፣ አድራሻ ፣ የድርጅቱ ማህተም ማሟላት ያለባቸው ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ22/09/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ታሽጎ በ4፡00 ሰዓት ግዥ ን/አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀን ውስጥ የዋጋውን 10% በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ /መሂ-1 በማስያዝ ውል መፈረም አለባቸው።
  11. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ ስራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪ አስይዘው ውል ካልፈረሙ መ/ቤቱ የጨረታ ማስከበሪያውን የመውረስ መብት አለው።
  12. መ/ቤቱ ከላይ በተራ ቀጥር 1-2 ለቀረቡት የጨረታ ሰነድ ማንኛውም ህጋዊ ተወዳዳሪ የሚወዳደርባቸውን የጨረታ ሰነዶች በጨረታ ሰነዱ ላይ የቀረቡት የግንባታ አይነትና ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን መሰረት የመሙላት ግዴታ አለበት፡፡
  13. አሸናፊው የአሸነፈበትን ግንባታ ከሚፈለግበት ቦታ ሰርቶ የማስረከብና ሂሳቡን በስሙ የማወራረድ ግዴታ አለበት።
  14. በጨረታው ቅሬታ ያላቸው ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተና ለአሸናፊው ከተለየ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ባለው ቅሬታቸውን ለሚመለከታቸው አካል ማቅረብ አለባቸው ከተጠቀሰው ቀን በኋላ የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት የለውም።
  15. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቀጥር 0334400416 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
  16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  17. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  18. የጨረታው መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡

 

በዋግ ኽምራ ዞን የሠቆጣ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት

 

Save Tender