የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በሀዋሳ ከተማ አስ/ ጤና መምሪያ ለሀራንፋማ ቤዚክ (ጤና ኬላ አዲስ ግንባታ) ሥራ በ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ያስፈለገ በመሆኑ በተዘጋጀው ዲዛይን ተጠቅሞ በዘርፉ ፈቃድ ካለው ድርጅቶች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ በሀዋሳ ከተማ አስ/ ጤና መምሪያ ለሀራንፋማ ቤዚክ (ጤና ኬላ አዲስ ግንባታ) ሥራ በ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ያስፈለገ በመሆኑ በተዘጋጀው ዲዛይን ተጠቅሞ በዘርፉ ፈቃድ ካለው ድርጅቶች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅት መወዳደር ይችላሉ፡-
- በኮንስትራክሽን ዘርፍ ደረጃ BC-5/GC -5 እና ከዚያ በላይ ፍቃድ ያላቸው፤ በሥራ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፤ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸዉ ፣
- የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀትና የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱን ከሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ/አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 /ሃምሳ አራት/ በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 /ለሃያ አንድ/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ወስዶ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲ.ፒ.አ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት።
- ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ኮፒ (ቴክኒካል እና ፋይናንሻል) በመያዝ ተከታታይ ቀናት በፋይ/ኢኮ/ልማ/ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 /ግዢ ኬዝ ቲም/ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ22ኛው ቀን 3፡00 ሰዓት ታሽጎ በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት 3፡30 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት ፤ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው በተመሣሣይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታ ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በሲዳማ ክልል እና ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ተመሳሳይ ሥራ በእጁ ላይ ካለና የሥራው አፈጻጸም 70% ካልደረሰ በጨረታ መወዳደር አይችልም፡፡ ሥራው 70% እና በላይ የደረሰ ከሆነ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታ አከፋፈት ስነ-ስርዓት የተነበበው ዋጋ እና በአርቲሜቲክ ቼክ በሚደረግበት ጊዜ በሁለቱ መካከል ከ2% (ከሁለት ፐርሰንት) በላይ ሆነ በታች ልዩነት ካለ ተጫራቹ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል፡፡
- ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበ የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደ ላይ ከአሥራ አምስት ፐርሠንት (15%) በላይ ከሆነ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል፡፡
- ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበ የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደታች ከአሥራ አምስት ፐርሠንት (15%) በታች ከሆነ ለእያንዳንዱ ሥራ ዝርዝር ተጨባጭ የወቅቱ ገበያ የዋጋ ትንተና (Direct Unite cost Analysis sheet) ማቅረብ የሚችል እና ለዚህም መ/ቤቱ የጠየቀውን የውል ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ ወይም መያዣ ገንዘብ መጠን ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 046-220-99-63/046-212-13-34
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
