በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት ዓሣ ሃብት ልማት ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በተፈቃደ በጀት ለኮምቦልቻ የእንስሳት ጤና - ላቦራቶሪ እና ለጎንደር የእንስሳት ኳራንቲን ማዕከል አገልግሎት የሚውል ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር እና የፕሪንተር ቀለም ከእነ ማድረሻው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ቁጥር 02/2017
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት ዓሣ ሃብት ልማት ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በተፈቃደ በጀት ለኮምቦልቻ የእንስሳት ጤና - ላቦራቶሪ እና ለጎንደር የእንስሳት ኳራንቲን ማዕከል አገልግሎት የሚውል ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር እና የፕሪንተር ቀለም ከእነ ማድረሻው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- የግብር ከፋይነት መለያ /ቲን/ ማቅረብ የሚችል
- አጠቃላይ የገንዘብ መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር እና 1 በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ. 1-4 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የፎቶ ኮፒ ከቴክኒካል ፕሮፖዛል ከኦርጅናል ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
- ስለጨረታው አጠቃላይ ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዟል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ መሸጫ ዋጋ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ሲሆን ቢሮ ቁጥር 14 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሚወዳደሩበት አቅርቦት የሚሞሉትን ማንኛውም ግብር ጨምሮ ለሎት 1 /አንድ/ 150,000/ አንድ መቶ ሺህ ብር እና ለሎት 2 /ሁለት/ 150,000 ብር/ አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር / ለሎት 3 /ሶስት/ 1000 /አንድ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንከ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።
- የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በሎት ጥቅል ዋጋ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ስርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ መሰረት የአንዱን የነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ ድምር በመሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ ቴክኒካል ፋይናንሻል ለየብቻ በማሸግ ሁሉቱንም በሌላ ትልቅ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አብክመ ግብርና ቢሮ ቁጥር 19 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን በአየር ላይ ይቆያል፡፡ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል። ቀኑ በዓል/ዝግ/ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው የሚሳተፋ አካላት ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 0582266431 በመደወል ወይም በፋክስ ቁጥር 0582262891 በመላክ ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ
