በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት አሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በተፈቀደለት በጀት ቢሮው አገልግሎት የሚውል ኤሌክትሮኒክስ ፈርኒቸር እና የፕሪንተር ቀለም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት አሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር:- 02/2017
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት አሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በተፈቀደለት በጀት ቢሮው አገልግሎት የሚውል ኤሌክትሮኒክስ ፈርኒቸር እና የፕሪንተር ቀለም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይነት መለያ /ቲን ነምበር/ ማቅረብ የሚችሉ፣
- አጠቃላይ የገንዘብ መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋገጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከቴክኒካል ፕሮፖዛል ከኦርጅናል ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ስለጨረታው አጠቃላይ ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዟል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ መሸጫ ዋጋ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ሲሆን ቢሮ ቁጥር 14 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሚወዳደሩበት አቅርቦት የሚሞሉትን ማንኛውም ግብር ጨምሮ ለሎት1፣ 150,000 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) እና ለሎት 2፣ 150,000 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ለሎት 3፣ 1000 (አንድ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።
- የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በሎት ጥቅል ዋጋ ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ስርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ መሰረት የአንዱን የነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ ድምር በመሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ ቴክኒካል ፋይናንሻል ለየብቻ በማሸግ ሁለቱንም በሌላ ትልቅ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አብክመ ግብርና ቢሮ ቢሮ ቁጥር 19 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን በአየር ላይ ይቆያል። በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፣ ሆኖም 16ኛ ቀን በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም።
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው የሚሳተፋ አካላት ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ /ማብራሪያ⁄ ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር፡- 058 -2-26-64-31 በመደወል ወይም በፋክስ ቁጥር 058-2-26-28-91 በመላክ ማግኘት ይችላሉ።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት አሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤ
