የማዕከላዊ ኢትጵያ ከልል መንግስት ትምህርት ቢሮ በ2017 ዓ.ም በዩኒሴፍ የትምህርት ድጋፍ ለ4 የልዩ ፍላጎት /አካቶ ድጋፍ መስጫ ማዕከላትን/ ለማደራጀት የሚያስፈልጉ የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶችን እንደዚሁም ለሚኒ-ሚዲያ አገልግሎት የሚውል እስፒከር እና የጽህፈት መሣሪያዎች ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Central Ethiopia Region Bureau of Education (የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የማዕከላዊ ኢትጵያ ከልል መንግስት ትምህርት ቢሮ በ2017 ዓ.ም በዩኒሴፍ የትምህርት ድጋፍ ለ4 የልዩ ፍላጎት /አካቶ ድጋፍ መስጫ ማዕከላትን/ ለማደራጀት የሚያስፈልጉ የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶችን እንደዚሁም ለሚኒ-ሚዲያ አገልግሎት የሚውል እስፒከር እና የጽህፈት መሣሪያዎች ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ሎት.01 የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶችና የአካል ድጋፍ መሳሪያዎች፤
ሎት.02 ኤሌክትሮኒክስ፡
ሎት.03 ፈርኒቸር እና የሞንቶሶሪ ሼልፎች፡
ሎት.04 የሞንቶሶሪ ቁሳቁሶች፡
ሎት.05 የስርዓተ ጾታ ጉዳዮች ምላሽ አሰጣጥ ዘዴ ማሰልጠኛ ማንዋል ህትመት፡
ሎት.06 እስፒከር /ለሚኒ-ሚዲያ/፡
ሎት.07 የጽህፈት መሣሪያዎች ግዥ፣
መስፈርት፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ በግብር ከፋይነት ተመዝግበው የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ እንዲሁም በአቅራቢዎች ዝርዝር የዘመኑን የግብር ግዴታ የተወጡበትን መረጃ አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል መንግስት ትምህርት ቢሮ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 05 በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ፋይናንሻል እና ቴክኒካል አንድ ኦርጂናል እና ኮፒ ለየብቻ ለይቶ በማሸግ ይህ ማስታውቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በቢሮው ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 05 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት ብር 10,000 ብር (አስር ሺህ ብር ብቻ) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ፤ በቼክ ወይም የባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች ወራቤ ከተማ ክልል ትምህርት ቢሮ ግዥና ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ድረስ ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት 8:00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- የውል ማስከበሪያ የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ7 ቀናት በኋላ ውሉን መፈረምና የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና አይነቶች ክፍያ በሚፈፀምበት የገንዘብ አይነት የውሉን ጠቅላላ ዋጋ 10% በውል ማስከበሪያነት ማስያዝ አለበት።
- ቢሮው ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በጨረታ ሰነዱ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ መጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በጨረታው ውድድር በአሸናፊው የተሰጠው ዋጋ ሳይቀየር እስከ 20% መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።
- የጨረታ ሰነዱ ፀንቶ የሚቆየው ለ45 ቀናት ብቻ ነው።
- መ/ቤቱ በጨረታው ላይ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 046-7-71-06-88 መደወል ይችላሉ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ትምህርት ቢሮ
