የአርዳይታ ግ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ በ2016/2017 የምርት ዘመን ያመረተውን ምርት ስንዴ እና ጽድ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አርዳይታ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኮሌጅ
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2017
የአርዳይታ ግ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ በ2016/2017 የምርት ዘመን ያመረተውን ምርት
1. ስንዴ
በኮሌጁ በራሱ ያመረተውን የጽድ ምርቶች ለመሸጥ ፈልጓል፡፡
- የጽድ ጣውላ
- የጽድ ሞራሌ
- የጽድ የጌጠጌጥ እንጨት
- የጽድ ጊንዲላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ጨረታውን ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች በሥራ /በንግድ/ መስኩ በዘመኑ 2017 የተገበረ ንግድ ፈቃድ ቲን ሰርተፍኬት፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና በተጨማሪም ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት በጨረታ መሳተፍ የምትችሉ ስለመሆናቸው በቅርብ ቀን የተሰጠ የድጋፍ ደብድቤ ማቅረብ የምትችሉ ሁሉ የጨረታ ሰነዱን ከኮሌጁ ሽያጭ ክፍል ቢሮ አርዳይታ ሀሣሣ ሰብል ተ/ሀ/ል/ማዕከል ቢሮ እና አዲስ አበባ 22 መዞሪያ አዲስ ሂይወት ሆስፒታል ፊት ለፊት የሚገኘው የኮሌጅ ጉዳይ ፈፃሚ ቢሮ ብር 200.00 / ሁለት መቶ ብር በመግዛት እና የምርቶቹን ናሙናውን በትክክል በማየት መጫረት ይችላሉ፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን እስከ 14/9/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ 22 መዞርያ አዲስ ሂይወት ሆስፒታል ፊት ለፊት የሚገኘው የኮሌጅ ጉዳይ ፈፃሚ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የመወዳደርያ ፖስታውን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዕለቱ 8፡00 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ታሽጎ በዕለቱ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ የኮሌጁ ጉዳይ ፈፃሚ ቢሮ ይከፈታል፡፡
በዚሁ መሠረት፡
- ለስንዴ ምርት የሲፒኦ መጠን ብር 1,044,900
- ለጣውላ፣ሞራሌ ፣ የጋርደን (የጌጠጌጥ) እንጨት እና ጊንዲ ምርት የሲፒኦ መጠን 100,000 ተመለከተ ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ CPO ብቻ ማቅረብ አለበት፡፡ ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0224760021 ወይም 0912241942
በሥራና ክሎት ሚኒስቴር የአርዳይታ ግ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ አርዳይታ
