በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው እንሰሳት ሀብት ተጠሪ ፅ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የእንሰሳት መድሃኒትና መሳሪያዎች በዘርፉ የተሰማሩ ጅምላ አቅራቢዎችን በማሳተፍና በማወዳደር ዝቅተኛ ዋጋ ከሰጠው ድርጅት አሸናፊ ተጫራቾች ጋር ውል በመፈፀም መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የሰ/ሸዋ ዞን የባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ዋና ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሱ፡-
- የዘመኑ የታደሰ የጅምላ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የብቃት ማረጋገጫ ማስረጃቸውን ማቅረብ የሚችሉ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን መሞላት የሚገባውን መረጃ ሁሉ በትክክል በመሙላት እና በመፈረም አንድ ኦሪጅናል ፖስታ የራሳቸውን ፊርማና አድራሻ ተፅፎበት በማሸግ ለእንሰሳት መድሃኒትና መሳሪያዎች አቅርቦት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከ2:30 እስከ 11፡ 30 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን ከባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመግዛት በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን በ4:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይታገድም፡፡
- ከተዘረዘሩት እቃዎች መካከል ከፋፍሎ መሙላት አይቻልም፤ ሁሉም እቃዎች መሞላት አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 20 መግዛት ይቻላል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም CPO ብር 8,000 (ስምንት ሺህ ብር) በባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የእንስሳት መድሃኒት እና መሳሪያዎች ለመሳተፍ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ጅምላ አከፋፋዮች ብቻ በጨረታው ላይ የሚሳተፉ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ በኋላ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ 10% የውል ማስከበሪያ በባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም ማስያዝ እና ውል መዋዋል ይኖርባቸዋል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-6-37-50-23 ደውለው መረዳት ይችላሉ፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የሰ/ሸዋ ዞን የባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ዋና ጽ/ቤት