የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ያገለገሉና የተጋቡ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
Metehara Sugar Factory (መተሐራ ስኳር ፋብሪካ)
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር MSFLP/01/2025
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ያገለገሉና የተጋቡ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
|
1 |
ቁርጥራጭ ብረታ ብረት |
ኪ.ግ |
2500,000 እስከ 300,000 |
|
2 |
ያገለገለ የመዳብ ሽቦ |
ኪ.ግ |
244 |
|
3 |
ያገለገለ የመኪና ጎማ |
ኪ.ግ |
5000 |
|
4 |
የተቃጠለ ዘይት |
በሊትር |
8320 |
|
5 |
ያገለገለ የነሃስ ቱቦ |
ኪ.ግ |
500 እስከ 1000 |
|
6 |
ያገለገለ የመኪና ባትሪ ባለ12-150AM |
በቁጥር |
47 |
|
7 |
ያገለገለ የመኪና ባትሪ ባለ12V-120AM |
በቁጥር |
7 |
|
8 |
ያገለገለ የመኪና ባትሪ ባለ12V-100AM |
በቁጥር |
64 |
|
9 |
ያገለገለ የመኪና ባትሪ ባለ12V-75AM |
በቁጥር |
12 |
|
10 |
ያገለገለ የመኪና ባትሪ ባለ12V-70AM |
በቁጥር |
69 |
|
11 |
ባዶ የግሪስ በርሜል ባለ ክዳን |
በቁጥር |
112 |
|
12 |
ባዶ የዘይት በርሜል |
በቁጥር |
294 |
- ከላይ በዝርዝር የቀረቡትን ያገለገሉና የተጋቡ ዕቃዎች ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሳተፍ የምትፈልጉ በዘርፉ አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሠርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፊኬት በማቅረብ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ሜክሲኮ ፊሊፕስ ህንፃ ግዥ ቡድን 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 215 ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ገዝተው በጨረታ መሳተፍ ይችላሉ፣
- ማንኛውም ተጫራች መግዛት የሚፈልገውን ያገለገሉና የተጋቡ ዕቃዎችን መተሐራ ስኳር ፋብሪካ ንብረት አስተዳደር ቡድን በግንባር በመቅረብ መመልከት ይችላል፣
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሠርተፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፊኬት እና ለጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የሚመርጧቸውን ዕቃዎች ጠቅላላ ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) በባንክ ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ማስያዝ አለባቸው፤
- ተጫራቾች፣ ከዚህ የጨረታ ሰነድ ጋር በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ሠንጠረዥ ዝርዝር ላይ የሚሰጡትን ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በትክክል በመሙላት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፣
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ በላዩ ላይ ሙሉ ስምና አድራሻ በመፃፍ ግንቦት 19 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ በ4፡00 ሰዓት በፊት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 119 ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ ከዚህ ሰዓት በኃላ የሚቀርብ የጨረታ ስነድ ተቀባይነት የለውም፣
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ተ.እ.ታ (VAT) የማይጨምር ሲሆን፣ የጨረታ አሸናፊዎች ለሚገዙት ዕቃ ተጨማሪ እሴት ታክስ የመክፈል ግዴታ አለባቸው፣
- ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራቾች ይኸው እንደተገለጸላቸው ያሸነፉበትን ሙሉ ዋጋ በቅድሚያ በመክፈል ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለጸበት ቀን አንስቶ በአሥር ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ ሲኖርባቸው! ይህ ባይሆን ግን ድርጅቱ ጨረታውን ሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያነት የተያዘውን ገንዘብ ለራሱ ገቢ የሚያደርግ መሆኑን ከወዲሁ ያሳውቃል፣
- ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ላይ ከላይ ከፍ ብሎ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 119 ውሰጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣
- ፋብሪካው ስለ አሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኝ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፡-
0115-505607, 0115-505633
ሜክሲኮ አደባባይ ፊሊፕስ ሕንፃ
አዲስ አበባ
በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ
