Tender Detail

Tender Details

  • Company የሞጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address ሞጆ ከተማ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0221161644
  • Website
  • Deadline28 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-28 00:00:00
  • Categories Generators

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሞጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለሞጆ ከተማ ማዘጋጃ ቤትና ለሞጆ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የሚውሉ ጀነሬተሮችን በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የሞጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሞጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለሞጆ ከተማ ማዘጋጃ ቤትና ለሞጆ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የሚውሉ ጀነሬተሮችን - በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ፡-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ፤ የዘመኑን ግብር ከፍሎ ማጠናቀቁንና ፣ ጨረታ ላይ እንዲሳተፍ የሚል ማስረጃ ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን ጽ/ቤት ማቅረብ አለበት።
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No.) የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሰውን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከሞጆ ከተማ ገንዘብ ፅ/ቤት በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላል፡፡
  7. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺ ብር) ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ ስራ ቀናት አየር ላይ ይቆያል።
  10. ጨረታው የሚከፈተው በጋዜጣ ከወጣበት በ 16ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሞጆ ከተማ ገንዘብ ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ውስጥ ይከፈታል። እለቱ በዓል ወይም መ/ቤቱ ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።
  11. የጨረታው አሸናፊ ዕቃዎችን እስከ ሞጆ ከተማ ገንዘብ ፅ/ቤት መጋዘን ድረስ በራሱ ወጪ አጓጉዘው ማቅረብ፣ መትከልና ኢንስታሌሽኑን መስራት አስተካክሎ መግጠም አለባቸው።
  12. የጨረታው አሸናፊ በጨረታ መመሪያ በተሰጠው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በውስጥ ማስታወቂያና በስልክ እንደተገለፀ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የጨረታ ውል ከሞጆ ከተማ ገንዘብ ፅ/ቤት ጋር መፈራረም አለበት። ይህ ባይፈጸም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ገቢ ይሆናል፡፡
  13. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0221161644 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

የሞጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender