Tender Detail

Tender Details

  • Company በጋሞ ዞን ምዕራብ ዓባያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት (ብርብር)
  • Address ብርብር ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046 452 0015
  • Website
  • Deadline26 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-26 00:00:00
  • Categories 3- Wheel Vehicle, Motorcycles And Bicycles , Electronics Materials

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን የምዕራብ ዓባያ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በጋሞ ዞን ምዕራብ ዓባያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት (ብርብር)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን የምዕራብ ዓባያ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

እነዚህም:-

1. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣

2. የተለያዩ ሞተር ሣይክሎች

ስለሆነም በዚሁ መሠረት:-

  1. በዘርፉ የንግድ ፍቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲነምበር) ያለው፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ፣ የአቅራቢነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ኦንላይን (በEgp) የተመዘገበ ፣
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ብር 10,000 እና የተለያዩ ሞተር ሣይክሎች ብር 10,000 በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠበት ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት በወረዳው ገቢዎች ባለሥልጣን ቅ/ጽ/ቤት በመቅረብ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ) ብቻ በመክፈል እና ደረሰኙን በመያዝ የጨረታውን ዝርዝር መረጃ የያዘውን ሰነድ ከወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ ፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናሉንና ኮፒውን ለየብቻ በማሸግ ሙሉ አድራሻውን በመግለጽ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን እንዲጨምሩ እያሳሰብን ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በወጣ በ16ኛው የሥራ ቀን በጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይታሸጋል፡፡
  5. ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ልክ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ ሥራ ቀን ላይ በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  6. አሸናፊ ድርጅት የጨረታ ሰነድ በተከፈተ በሰባተኛው ቀን የውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ ውል ይፈራረማል፡፡
  7. የጨረታው ሣጥን ምዕራብ ዓባያ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 11 ይገኛል፡፡
  8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0464520015/0464520009

 

በጋሞ ዞን ምዕራብ ዓባያ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት

ብርብር

 

Save Tender