የድሬዳዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ግዢና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ለ2017 በጀት ዓመት UPS (10KVA) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎች እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ግዢና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የድሬዳዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ግዢና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ለ2017 በጀት ዓመት UPS (10KVA) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎች እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN NO ያላቸው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- በዘርፉ የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው
- የታተመ ቁጥር ያለው ደረሰኝ፣
- የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው ያላት
- በራሱ ትራንስፖርት ቢሮ ድረስ ማምጣት የሚችል
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000 /ሰላሳ ሺ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ /cpo/ ማስያዝ የሚችል ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሆኖ በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ዘወትር በሥራ ሰዓት በድሬዳዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ግዢ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቢሮ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 303 በመቅረብ የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመግዛት የሚጫረቱበትን ዋጋ ሞልተው በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር ይችላሉ።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት ታሽጎ በዛው እለት ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ግዢና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 303 3ኛ ፎቅ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የጨረታ መክፈቻው ቀን በበዓል ቀናት ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ - በስልክ ቁጥር 09-13-28-26-37 / 09-10-25-82-50 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ግዢና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
