የቴፒ ከተማ ጤና አ/ጣቢያ 2017 በጀት አመት በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ መድኃኒትና የህክምና ቁሳቁሶችን መግዛት ይፈልጋል፡፡
በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የቴፒ ከተማ ጤና አ/ጣቢያ 2017 በጀት አመት በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ መድኃኒትና የህክምና ቁሳቁሶችን መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁም መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል።
- ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ ለ2017 የታደሰ የንግድ ፈቃድ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ተመዝጋቢ የሆኑበትን ሰርተፍኬት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በተሰማሩበትሥራ ዘርፍ በሚመለከተው አካል ከኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የተሠጠ ፍቃድ /የሙያ ብቃት ማረጋገጫ/ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች 2017 ዓ.ም ግብር ስለመክፈላቸው የሚገልጽ የገቢ ክሊራንስ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ሲያቀርቡ ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን 10,000 /አስር ሺህ ብር/ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ቴ/ከ/ጤ/አ/ጣቢያ በደረሰኝ RV/በመቁረጥ ማስያዝ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች መ/ቤቱ የሚያቀርበው ዋጋ መሙያ የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበትና ተፈርሞበት የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ ተደርጎበት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ 1(አንድ) ኦርጅናል ፖስታና ሁለት ኮፒ ፖስታ በማድረግ በዕለቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
- ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ቴፒ ከተማ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ በመቅረብ ቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈው ተጫራች ያሸነፈበትን መድሃኒቶችንና የህክምና ቁሳቁሶችን ቴፒ ከተማ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ድረስ አጓጉዞ ማስረከብ አለበት፡፡
- ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሰራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ ከጠዋቱ ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡ በእለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው ስራ ቀን ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ መክፈቻው ቀን ካልተገኘ የመ/ቤቱ የጨረታ ኮሚቴ ጨረታውን የመክፈት ሙበቱ የተጠበቀ ነው።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ
