የሀዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት ባቀዱት መሠረት የሀዋሳ ከተማ ቄራ አገልግሎት የስጋ ማመላለሻ ኮንቴነር መኪናዎችን ብዛታቸው 6 /ስድስት/ የሆኑትን ውጫዊ አካል Body /Van/ እና ውስጣዊ አካል Almunium Sheet በጨረታ አወዳድሮ ማስጠገን ይፈልጋል፡፡
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
ጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት ባቀዱት መሠረት የሀዋሳ ከተማ ቄራ አገልግሎት የስጋ ማመላለሻ ኮንቴነር መኪናዎችን ብዛታቸው 6 /ስድስት/ የሆኑትን ውጫዊ አካል Body /Van/ እና ውስጣዊ አካል Almunium Sheet በጨረታ አወዳድሮ ማስጠገን ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ጋራዦች መወዳደር ይችላሉ፡-
- በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፤
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸዉ ፤
- የጋራዥ ህጋዊ የሥራ ፈቃድ ሠርተፊኬት ከመን/ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ የተሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የታደሰውን ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት ።
- የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ለአስራ አምስት ቀናትን / ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም በፋይ/ኢኮ/ልማ/ መምሪያ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ16ተኛዉ ቀን ከቀኑ 3፡15 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከቀኑ 3፡45 ሠዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል ፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ስልክ ቁጥር 046-212-13-34
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
ሀዋሳ
