Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ
  • Address የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወራቤ ቅርንጫፍ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ : በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት : ኢትዮጵያ, Phone: 0467 71 11 80
  • Website
  • Deadline23 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-23 00:00:00
  • Categories Generators , Electronics Materials

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ለቢሮው ስራ የሚያገለግል ጄኔሬተርና ቴሌቭዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ለቢሮው ስራ የሚያገለግል ጄኔሬተርና ቴሌቭዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው /ያላቸው ፤
  3. በፋይናንስ መስሪያ ቤቶች በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ እና በህግ ያልተገደበ ፤
  4. ለእያንዳንዱ ዕቃ ግዥ በቢሮው የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከቢሮው የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 10 በመቅረብ የማይመለስ ብር 300 በመክፈል መግዛት ይቻላሉ፤
  5. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የቴክኒካል የጨረታ ሰነድና የፋይናንሻል የጨረታ ሰነድን ለየብቻ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለእያንዳንዱ ተመሳሳይ አንድ አንድ ኮፒዎች አዘጋጅተው በየኤንቨሎፑ የውጭ ገጽ ዋና (ኦርጂናል) ወይም ኮፒ ብሎ በመፃፍና አሽገው ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. በማንኛውም ኤንቬሎፕ ውስጥ የጨረታ ማስከበሪያ ማስገባት ያለባቸው ለምሳሌ ተጫራቾች የንግድ ፍቃድ፣ የቫት ሰነድ መልካም አፈጻጸም ወዘተ መካተት ያለባቸው በቴክኒክ የጨረታ ሰነድ በሆኑት በዋናው ኦሪጅናል እና ኮፒ ተብሎ በተገለጹት በሁለቱም ኤንቬሎፕ ሲሆን በፋይናንስ የጨረታ ሰነድ በዋናው /ኦሪጅናል ሆነ ኮፒ ኤንቬሎፕ ውስጥ ከፋይናንስ የጨረታ ሰነድ ውጭ ምንም ተጨማሪ መረጃ ማስገባት አይፈቀድም፤
  7. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን የሚያስገቡበት የመጨረሻ ቀን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ብቻ ሰነዱ የሚሸጥ ይሆናል። ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮው በግልጽ ይከፈታል። ሆኖም 15ኛ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚዘጋውና የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይሆናል።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ CPO የባንክ ጋራንቲ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  9. ቢሮው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
  10. የጄኔሬተርና ቴሌቭዥን ዝርዝር መረጃ ከጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተያያዘና የተገለጸ በመሆኑ ዝርዝሩን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

አድራሻ፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወራቤ ቅርንጫፍ ህንፃ 1ኛ ፎቅ

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ

 

Save Tender