በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ በዳውሮ ዞን የታርጫ ጠቅላላ ሆስፒታል ከሆስፒታሉ ቋሚ ንብረቶች መካከል በተለያዩ ምክንያቶች የተወገዱ: የአዋቂና የህፃናት መኝታ የሴቶች ማዋለጃና እንዲሁም የቀዶ ጥገና ህክምና መስጫ አልጋዎች የመመርመሪያ ኮች፣ የዕቃ ማስቀመጫ ባለላሜራ ሎከር፣ የዕቃ ማጓጓዣ ጋሪ፣ የመብራት ፕሎረስንት አቃፊ ብረቶችን፣ የቤት ክዳን አላቂ ቆርቆሮዎችን፣ የየሥራ ክፍሉ መብራት ተሸካሚ ብረቶችን፣ ያገለገሉ አሮጌ ጎማዎችንና የመኪና ባትሪዎችን፣ የተለያዩ ጉማጅ ብረታ ብረቶችንና የቀድሞ ሞድ ቴሌቭዥኖችን በጨረታ ሰነዱ በተዘረዘረው ዝርዝር መሰረት ለፈላጊዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ በዳውሮ ዞን የታርጫ ጠቅላላ ሆስፒታል
የአሮጌ ዕቃ ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ በዳውሮ ዞን የታርጫ ጠቅላላ ሆስፒታል ከሆስፒታሉ ቋሚ ንብረቶች መካከል በተለያዩ ምክንያቶች የተወገዱ: የአዋቂና የህፃናት መኝታ የሴቶች ማዋለጃና እንዲሁም የቀዶ ጥገና ህክምና መስጫ አልጋዎች የመመርመሪያ ኮች፣ የዕቃ ማስቀመጫ ባለላሜራ ሎከር፣ የዕቃ ማጓጓዣ ጋሪ፣ የመብራት ፕሎረስንት አቃፊ ብረቶችን፣ የቤት ክዳን አላቂ ቆርቆሮዎችን፣ የየሥራ ክፍሉ መብራት ተሸካሚ ብረቶችን፣ ያገለገሉ አሮጌ ጎማዎችንና የመኪና ባትሪዎችን፣ የተለያዩ ጉማጅ ብረታ ብረቶችንና የቀድሞ ሞድ ቴሌቭዥኖችን በጨረታ ሰነዱ በተዘረዘረው ዝርዝር መሰረት ለፈላጊዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልቶ ሊወዳደር ይችላል፡፡
1ኛ በዘርፉ የታደሰና ህጋዊ የሆነ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣
2ኛ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው
3ኛ የቫት ተመዝጋቢነት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ እና እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ብር 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር/ ማስያዝ አለበት፡፡ ገንዘቡ ለጨረታ አሸናፈዎች ከግዥ ዋጋ ጋር ይደመርላቸዋል፡፡ ለተሸናፊዎች የጨረታ ውጤቱ እንደፀደቀ ይመለስለታል፡፡ የጨረታ አሸናፊ ዕቃውን ጨረታው ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናቶች ውስጥ ሂሳቡን ከፍሎ በመንግስት የሥራ ሰዓት በአንዴ ማንሳት አለበት:: በተባለው ቀን ካላነሣ ለቆየባቸው ለእያንዳንዱ ቀናት የኢት/ያ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ የቦታ ኪራይ ለተቋሙ ይከፍላል፡፡ አሸናፊው ድርጅት መሆኑን ተገልጾ ካልቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) አይመለስለትም በሁለተኛ ለወጣው በአንደኛ በወጣው ዋጋ ይሸጣል፡፡ ከላይ የተዘረዘሩ ቅድመ ሁኔታዎችን ያሟላ ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ከታርጫ ጠቅላላ ሆስፒታል የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የሥራ ክፍል የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ከፍሎ በመንግስት የሥራ ሠዓት መውሰድ ይችላል፡፡ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናቶች ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ በ16ኛ ቀኑ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ይህንን ጨረታ ሙሉ በሙሉ/ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት ይከናወናል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች ብዛት ሊጨምር /ሊቀንስ ይችላል፡፡ ክፍያውም ባለውና በተረከበው ዕቃ ልክ ይሆናል፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያ ስለጨረታ ካስፈለገዎ ስልከ ቁጥር፡- 09-12-42-37-79/ 09-17-83-24-38 ይደውሉ፡፡
በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ በዳውሮ ዞን የታርጫ ጠቅላላ ሆስፒታል
