የሲዳማ ብ/ክ/መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከዚህ በታች በየሎቱ የተዘረዘሩትን ነገሮች ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የሲዳማ ብ/ክ/መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብ/ክ/መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከዚህ በታች የተመለከተውን
- ሎት 1 ለአዲስ ቢሮ የሚሆን የተለያዩ አጠቃላይ የቢሮ ፈርኒቸር፤
- ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ፣
- ሎት 3 መጋረጃና ምንጣፍ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች በዝርዝር የተመለከቱ ሁኔታዎችን በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡-
- ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸዉ፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና የግብር ከፋይ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት በባንክ በተረጋገጠ cpo 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ) ብር ማስያዝ አለባቸው።
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብር ብቻ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000342552424 በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ የታደሰ ንግድ ፍቃድና ተያያዥነት ያላቸዉ ሰነዶች ኮፒ ይዞ በመቅረብ ከግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 3ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 310 ቀርበዉ ሰነዱን ማግኘት ይችላል፡፡
- የተፈለገው በተለይ ሎት 1 የተለያዩ የቢሮ ፈርኒቸር ለአዲሱ ር/መስተዳደር ቢሮ በመሆኑ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በሀርድ ኮፒ እና በሲዲ ወይም በቴሌግራም አማራጭ ሶፍት ኮፒ በመውሰድ ቪድዮውን በጥንቃቄ በመመልከት አጠቃላይ የተፈለገው የቢሮ ፈርኒቸር ዓይነትና ጥራት ዘመናዊና ወቅታዊ መሆኑን በጥንቃቄ የመ/ቤቱን ፍላጎትና በሰነዱ ላይ በመመልከት የተፈለገውን በመረዳት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመሪያ መሰረት ተሞልቶ ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ በሰም በታሸገ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ከተውና በሁሉም ዶክመንት የድርጅቱን ማህተም በመምታትና በመፈረም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 እስከ 8፡30 ሰዓት ድረስ ለዚህ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ በሲዳማ ብ/ክ/መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት 9፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ያሸነፉበትን ዕቃ እስከ ሲዳማ ብ/ክ/መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ቢሮ በማቅረብ ያስረክባል/ይገጥማል ። በተጨማሪም አሸናፊ ድርጅት አስቀድሞ የዕቃዉን ናሙና ማቅረብና ማሳየት ከቢሮው ጋር መተማመን ይኖርበታል።
- ጨረታው የሚከፈትበት የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይሆናል። ዝርዝር የጨረታ ሂደት በጨረታዉ ሰነድ መመሪያ ላይ ተገልጧል፡፡
ቢሮዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የሲዳማ ብ/ክ/መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት
