Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ክልል ሰ/ሸዋ ዞን በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ የአመድጉያ የበግ ብዜትና ዝሪያ ማሻሻያ ማዕከል
  • Address ሰሜን ሸዋ ዞን ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-12-16-65-55
  • Website
  • Deadline21 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-22 00:00:00
  • Categories Pharmaceutical Products , Health Care, Medical Industry Materials And Machinery

የአመድጉያ የበግ ብዜትና ዝሪያ ማሻሻያ ማዕከል ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን መሪ የ2017 በጀት ዓመት የበጎች መደሃኒት እና የህክምና መገልገያ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአማራ ክልል ሰ/ሸዋ ዞን በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ የአመድጉያ የበግ ብዜትና ዝሪያ ማሻሻያ ማዕከል


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአመድጉያ የበግ ብዜትና ዝሪያ ማሻሻያ ማዕከል ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን መሪ የ2017 በጀት ዓመት የበጎች መደሃኒት እና የህክምና መገልገያ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ የንግድ ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. ተጫራቾች የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
  4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN Number/ ተመዝጋቢና ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
  5. ጠቅላላ ግዥው ወይም ዋጋው ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢና ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
  6. ተጫራቾች ጨረታውን መ/ቤቱ እንደ አስፈላጊነቱ በተናጠል ዋጋም ሆነ በጥቅል ወይም በሎት መ/ቤቱ የሚያወዳድር መሆኑን ማወቅ አለባቸው።
  7. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታችውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒውንና ኦርጅናል ሰነዶቻቸውን ማቅረብና ማመሳከር ይኖርባቸዋል፡፡
  8. የሚገዙ የበግ መድሀኒቶች እና የህክምና መገልገያ ዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር ስፔስፊኬሽን መ/ቤታችን በአማረኛ ቋንቋ ያዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 50 (ሃምሳ ብር) በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 5 መውሰድ ይቻላል፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦድ /ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችል እና በጨረታው ላይ ችግር ቢከሰትና ጨረታውን ካሸነፈ በኋላ በራሱ ምክንያት ውል ባይፈፅም ያስያዘውን 2% የሚውርስ መሆኑንና አቅርቦቱን ካሸነፈ ለውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሁለት ኮፒ የሚመለከታቸውን ሰነዶች በሙሉ በማድረግ ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ ማቅረብ አለባቸው።
  11. የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በእለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ይታሸጋል፡፡
  12. የጨረታ ሳጥኑ በማግስቱ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማዕከላችን በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 3 ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  13. ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም ጽ/ቤቱ ጨረታውን የሚከፍት ይሆናል፡፡
  14. መ/ ቤታችን ከሚገዛው እቃ 20% /ሃያ ፐርሰንት/መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
  15. ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  16. በተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09-12-16-65-55 / 09-23-46-97-31 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

በአማራ ክልል ሰ/ሸዋ ዞን በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ አመድ-ጉያ የበግ/ብ/ዝ/ማ/ማእከል

 

Save Tender