Tender Detail

Tender Details

  • Deadline23 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-23 00:00:00
  • Categories Electronics Materials

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ጎንደር ዞን አስተዳደር የበየዳ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ/ቡድን በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለወረዳው ሲ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ኤሌክትሮኒክስ ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ በዘርፉ ንግድ ፍቃድ ያላቸውን ተጫራቾች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ጎንደር ዞን አስተዳደር የበየዳ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ/ቡድን በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለወረዳው ሲ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ኤሌክትሮኒክስ ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ በዘርፉ ንግድ ፍቃድ ያላቸውን ተጫራቾች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው።
  3. ግዡ ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ እቃዎች ዓይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጽ/ቤቱ መ/ሂ 1 ማስያዝ የሚችል እና አሸናፊ ከሆነ በኋላ ከጠቅላላ ዋጋው 10% የውል ማስከበሪያ ዋስትና ፤ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጽ/ቤቱ መ/ሂ 1 ማስያዝ የሚችል፡፡
  7. አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ውል የሚወስደው በበየዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ/ቡድን እና ፍትህ ጽ/ቤት ይሆናል፡፡ አሸናፊ የሚለየው በጠቅላላ ድምር መሆኑን የተረዳ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት በበየዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ዘወትር እሁድና ቅዳሜን ጨምሮ እስከ 11፡30 በመምጣት የማይመለስ 150 /አንድ መቶ ሃምሳ /ብር ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ትችላላችህ፡፡
  8. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በአስራ ስድስተኛ ቀን 8፡00 ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ህጋዊ ተጫራቾች /ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈትበት እና የሚታሸግበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ / ካላንደር ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን 8፡00 ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ህጋዊ ተጫራቾች /ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት የጨረታ ሣጥኑ ታሽጎ ይከፈታል፡፡
  9. የጨረታ አሸናፊው እቃዎቹን በበየዳ ወረዳ ድል-ይብዛ ከተማ ግብርናና አስተዳደር ንብረት መጋዘን ማቅረብ የሚችል እና ማውረጃ እና መጫኛ በተጫራቹ መሸፈን የሚችል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. የጨረታ ሰነዱን በተሰጠው ዝርዝር መሰረት ስርዝ ድልዝ በሌለው መሙላት የሚችል፡፡
  12. በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚመታው ማሕተም ከንግድ ፍቃድ ጋር ቀጥተኛ / ተዛማጅ የሆነ መሆን አለበት።
  13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 20 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በተጫራቾች መመሪያ ወይም በስልክ ቁጥር 0975643488 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ጎንደር ዞን አስተዳደር የበየዳ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ/ቡድን

 

Save Tender