Tender Detail

Tender Details

  • Company South Ethiopia Regional Health Bureau (የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ)
  • Address ጂንካ ፡ኢትዯጵያ, Phone: - - - - - -
  • Websitehttps://serhb.gov.et/
  • Deadline23 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-23 00:00:00
  • Categories Printing And Publishing , Furniture , Stationery Materials , Electronics Materials

የደቡብ ኢትዮጵያ ክ/መ/ጤና ቢሮ ለሁሉም ስራ ሂደቶች እና ፕሮግራሞች እንዲሁም አገልግሎት በሚሰጥባቸው ህክምና ተቋማት እና ሌሎች መዋቅሮች ለክትትልና ግምገማ ምቹ ለማድረግ ሎት1. ህትመት፣ ሎት 2. ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 3 እስቴሽነሪ፤ ሎት 4. ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

South Ethiopia Regional Health Bureau (የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ)


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የደቡብ ኢትዮጵያ ክ/መ/ጤና ቢሮ ለሁሉም ስራ ሂደቶች እና ፕሮግራሞች እንዲሁም አገልግሎት በሚሰጥባቸው ህክምና ተቋማት እና ሌሎች መዋቅሮች ለክትትልና ግምገማ ምቹ ለማድረግ ሎት1. ህትመት፣ ሎት 2. ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 3 እስቴሽነሪ፤ ሎት 4. ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚሁ መሠረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ብቃት ያላቸው ተጫራች ድርጅቶች ከዚህ በታች ያለውን መስፈርት የምታሟሉ በሙሉ መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፦

  1. በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ
  2. በመንግስት ዕቃ ወይም አገልግሎት አቅራቢነት የተመዘገቡ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በእያንዳንዱ 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/ በቢሮው ስም አዘጋጅቶ ማቅረብ አለበት፡፡
  3. ተጫራቾች ከዚህ በፊት በመስኩ አገልግሎት የሰጡበትን የመልካም ስራ አፈጻጸም የምስክር ወረቀት ከመንግስታዊ መ/ቤት ወይም ተቋማትና ከሌሎች ህጋዊ ዕውቅና ካላቸው ድርጅቶች ቢያንስ 1/ ከዚያ በላይ / ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. በጨረታው የሚሳተፉ ድርጅቶች ለሚያቀርቡት ዕቃ ወይም አገልግሎት ጥራት በሚመለከት ናሙና እንዲያቀርቡ በጨረታው ሠነድ ላይ ሊጠየቅ ይችላል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15ኛ ቀን 11፡00 ድረስ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ቢሮ ቁጥር 8 ፋይናንስ ክፍል መግዛት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሠነዱንና አስፈላጊውን መረጃ አሟልተው አንድ ኦርጅናል ቴክኒካልና ፋይናንሻል እንዲሁም ሁለት ቅጅዎችን ፋይናንሻልና ቴክኒካል ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውንና ስልክ ቁጥራቸውን በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ዕለት አንስቶ ተከታታይ 15 ቀናት በመቁጠር እስከ 16ኛው ቀን 6፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ታሽጐ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡00 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የመንግስት የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 08 ይከፈታል፣
  7. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ በሙሉም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁ. 0916334317/0916315871/ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

የደቡብ ኢትዮጵያ ክ/መ/ጤና ቢሮ

 

Save Tender