Tender Detail

Tender Details


በየካ ክ/ከ የወ01 ጤና ጣቢያ በ2017 በጀት አመት በመንግስት ከተመደበለት ትሬዠሪና የውስጥ ገቢ መደበኛ በጀት በ2ኛ ዙር ብሄራዊ ግልፅ ጨረታ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን መድሀኒቶችን እና የህክምና መሳሪያዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በየካ ክ/ከ የወ01 ጤና ጣቢያ በ2017 በጀት አመት በመንግስት ከተመደበለት ትሬዠሪና የውስጥ ገቢ መደበኛ በጀት በ2ኛ ዙር ብሄራዊ ግልፅ ጨረታ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን መድሀኒቶችን እና የህክምና መሳሪያዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. መድሀኒት እና የህክምና መሳሪያ ግዥ እና የጀኔሬተር ሙሉ ሰርቪስ
  2. የተለያዩ ያገለገሉ እቃዎችን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ 1/ የተሰባበሩ ወንበሮች የብረት እና የእንጨት 2/ ፋይል ካቢኔቶች ፍሎረሰንት አቃፊ 4/ ላተራል 5/ የተሰባበረ ጠረጴዛ 6/ ተሽከርካሪ ወንበር 7/ የተሰባበረ የቧንቧ 8/ ካዝና 9/ ፋይል መደርደሪያ 10/ የተሰባበረ ኮመዲና የመሳሰሉት በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች፡-
  1. የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፤ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. በዘርፉ ለተወዳዳሪነት የተፈቀደበት የምዝገባ ማስረጃቸውን ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ ብር ብቻ በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው የስራ ቀን 3፡00 ሰዓት ድረስ ከተቋሙ ግዥ ክፍል መውሰድ የምትችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነዱ ላይ የሚጫረቱበትን ዋጋ ከነ ቫት በመሙላት እና ስም ፤ፊርማና የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም በማድረግ ዋናውንና ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ በተቋሙ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲ.ፒ.አ/ ብር 7000.00 /ሰባት ሺህ ብር/ ብቻ በማሰራት ዋናውን / ኦርጅናል ከሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው::
  5. ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን 3፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በይፋ ይከፈታል፡፡
  6. መድሀኒቶቹ እና የህክምና መመሪያዎች በተሰጠው ስፔስፊኬሽን መሰረት መቅረብ አለባቸው። ኤክስፓየርድ ዴት ለሚያስፈልጋቸው የተመረቱባቸውና ኤክስፓየርድ ጊዜያቸው በግልጽ የሚታይ መሆን አለባቸው የአገልግሎት ጊዜያቸው ቢያንስ አንድ ዓመት እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸው።
  7. ዋጋችሁን ስትሞሉ የምትሞሉትን ዋጋ ጠቅላላ ድምር እንድታስቀምጡ፡፡
  8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ ፡- ፈረንሳይ ወደ አርባ አንድ እየሱስ በሚያስገባው መንገድ ገባ ብሎ ከወረዳ 01 አስተዳደር ጽ/ቤት አጠገብ፡፡

ለበለጠ መረጃ:- ስ.ቁ 0111-548454/011-549680

 

የካ ክ/ከ የወ 01 ጤና ጣቢያ

 

Save Tender