Tender Detail

Tender Details

  • Company የደብረብርሃን የበግ ብዜትና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል
  • Address ደብረብርሃን ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116811463
  • Website
  • Deadline21 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-21 00:00:00
  • Categories Animals , Animal Feed And Supply , Supply Of Animals

የደ/ብርሃን የበግ ብዜትና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የተመጣጠነ የበጎች መኖ እና የወተት ላሞች የተመጣጠነ መኖ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የደብረብርሃን የበግ ብዜትና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የደ/ብርሃን የበግ ብዜትና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የተመጣጠነ የበጎች መኖ እና የወተት ላሞች የተመጣጠነ መኖ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ፡-

  • በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በዘርፉ አግባብ ያለው የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ከፌዴራል መኖ እንስሳትና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች በዘርፉ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ደ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በመግዛት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ተከታታይ የካላንደር ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የሚሸጡበትን ዋጋ በመሙላት እና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒውን በማያያዝና በፖስታ በማሸግ በደ/ብርሃን የበግ ብዜትና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው። ጨረታውን በዚሁ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  • ተጫራቾች የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ ከ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • የጨረታ ማስከበሪያ በቁርጥ ብር 15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በማስያዝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  • ተወዳድረው ያሸነፉ ድርጅቶች ያሸነፉትን ንብረት ሁሉንም ወጪውን ችሎ ማዕከሉ ድረስ አምጥቶ ማስረከብ አለበት፡፡
  • ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
  • የቫት ተመዝጋቢዎች 50%ቱን ቀንሰን የምናስቀር መሆኑን እንገልፃለን ፡፡
  • የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከናወናል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡-

ስልክ ቁጥር 0116811463 ወይም 0116812330 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የደ/ብርሃን የበግ ብዜትና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል

 

Save Tender