Tender Detail

Tender Details

  • Company Al-Afia Share Company (አል-ዓፊያ አክሲዮን ማህበር)
  • Address Bethel Square, Soyam Mall Building 5th Floor : Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 09-30-01-23-74
  • Websitehttps://alafiasc.com/
  • Deadline16 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-16 00:00:00
  • Categories Vehicle

የአል-ዓፊያ አክሲዮን ማህበር 2 ቶዮታ (Toyota Hatch back) ተሽከርካሪዎች ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳደሮ መሸጥ ይፈልጋል።

Al-Afia Share Company (አል-ዓፊያ አክሲዮን ማህበር)


 

ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር ፡- 01/2017

 

የአል-ዓፊያ አክሲዮን ማህበር 2 ቶዮታ (Toyota Hatch back) ተሽከርካሪዎች ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳደሮ መሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ጨረታውን መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከዚህ በታች በተመለከተው የጨረታ መመሪያ መሰረት መሳተፍ ይችላል፡፡

  1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 8 ባሉ የሥራ ቀናቶች ውስጥ ቤቴል አካባቢ በሚገኘው አል ዓፊያ አክሲዮን ማህበር ዋና ፅ/ቤት ሶያም ሞል 5 ተኛ ፎቅ በአካል በመቅረብና ተሸከርካሪዎቹን የሚዝዙበትን ዋጋ የሞሉበት የጨረታ ሰነዳቸውን በማስገባት መጫረት ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች ተሽከርካሪዎቹ ያሉበትን ሁኔታ ከላይ በተራ ቁጥር 1 ስር በተጠቀሰው አድራሻ በመገኘት በሰራ ቀናት ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት መመልከት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን ተሸከርካሪ በመለየትና የሚጫረቱበትን ዋጋ የዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት አንድ ተሸከርካሪ 20% በአል-ዓፊያ አክሲዮን ማህበር ስም በባንክ በተረጋጋጠ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ከጨረታ ዋጋ ማቅረቢያው ጋር በማያያዝ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው ግንቦት 8/2017 ዓ.ም ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ባሉበት ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቻው በተገኙበት በአል-ዓፊያ አከሲዮን ማህበር ዋናው ቢሮ ይከፈታል።
  6. የጨረታው አሸናፊ በግልፅ ማስታወቂያ ሠሌዳ ላይ ከተገለፀበት ዕለት ጀምሮ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ የሚፈለግበትን ክፍያ በመከፈል ተሸከርካሪውን መረከብ ይኖርበታል፡፡ በዚሁ መሠረት የማይፈፅም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለአክሲዮን ማህበሩ ገቢ ሆኖ አሸናፊነቱም ይሰረዛል፡፡
  7. በዚህ ጨረታ አሸናፊ የሚሆኑት ተጫራቾች የባለቤትነት ስም ዝውውር ጋር የተያያዙ ክፍያዎችን በመፈፀም ተሸከርካሪውን ይረከባሉ፡፡
  8. በጨረታው ተሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሰያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ (ቦንድ) የጨረታው አሸናፊዎች የሚፈለግባቸውን ክፍያ እንዳጠናቀቁ የሚመለስላቸው ሲሆን በጨረታው አሸናፊ ለሆነ ተጫራቾች ያስያዙትን ገንዘብ ከቀሪው ክፍያ ጋር ተደምሮ የሚታሰብላቸው ይሆናል፡፡
  9. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ቤቴል አደባባይ ተቅዋ መስጂድ ፊት ለፊት ሶያም ሞል 5ኛ ፎቅ ስልክ 09-30-01-23-74

 

አል-ዓፊያ አክሲዮን ማህበር

 

Save Tender