Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሄራዊ ክልል መንግስት በምዕራብ ጎንደር ዞን የአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት
  • Address ምዕራብ ጎንደር : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0918 606 804
  • Website
  • Deadline21 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-21 00:00:00
  • Categories Construction Vehicle

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በምዕራብ ጎንደር ዞን የአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/ አስ/ቡድን አማካኝነት የ2017 ዓ.ም በመደበኛ በጀት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ከተማዎች እና ለቀበሌዎች ለልማት አገልግሎት የሚውል ሎደር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልል መንግስት በምዕራብ ጎንደር ዞን የአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት


 

በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በምዕራብ ጎንደር ዞን የአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/ አስ/ቡድን አማካኝነት የ2017 ዓ.ም በመደበኛ በጀት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ከተማዎች እና ለቀበሌዎች ለልማት አገልግሎት የሚውል ሎደር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ያላቸው።
  2. ግብይቱ ከ200,000 ሺ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባችኋል፤
  3. ከሁሉም የጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማ መኖር አለበት ስርዝ ድልዝ ካለው በፊርማ መረጋገጥ አለበት የሚያቀርቡት የንግድ ፈቃድና ቲን ነምበር ግልፅና የሚነበብ መሆን አለበት።
  4. በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500 ብር እያንዳንዱን በደረጃ /በሎት/ ተለይቶ የቀረበውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. የጨረታ ሰነዱን መግዛት ለሚፈልጉ ተጫራቾች በአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት የግ/ን/አስ/ ቡድን አማካኝነት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 ቀናት በአየር ላይ ይውላል።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የጨረታ አይነት የዋጋውን 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዛዝ (CPO) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
  8. የሚገዛው የሎደር አይነትና ዝርዝር መግለጫ እስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነድ ጋር ማግኘት የሚችሉ ይሆናል።
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማቅረብ አዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 16ኛው ቀን 9፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በ16ኛው ቀን በ9፡30 ታሽጎ በዚሁ ቀን ከ10፡00 ሰዓት ጀምሮ ይከፈታል ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
  11. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ሎደር ጠቅላላ ዋጋ 10% በማስያዝ ውል መውሰድና ሎደሩን አ/አ/ጫ/ወ/አምጥቶ ማስረከብ አለበት።
  12. መ/ቤቱ የሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአ/አ/ጫ/ወ/ግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0918739709,0918606804/0922718368 የሚፈልጉትን ማስረጃ ማግኘት ይችላሉ።

 

ማሳሰቢያ፡- ከዚህ በፊት በየትኛውም ደረጃ በነበራቸው የአፈፃፀም ችግር ምክኒያት የታገዱ ወይም የእቃ አቅርቦት ችግር ያለባቸው አቅራቢዎችን አይጋብዝም፡፡

 

በምዕራብ ጎንደር ዞን የአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ገንዘብ ጽሕፈት ቤት

 

Save Tender