የሆሣዕና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ በ2017 ዓ/ም ለኮሌጁ ሥራ አገልግሎት የሚውል ሎት1 ኤሌክትሮኒክስ እና ሎት 2 የኤሌክትሪክና የጥገና ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የሆሣዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
የጨረታ ማስታወቂያ
የሆሣዕና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ በ2017 ዓ/ም ለኮሌጁ ሥራ አገልግሎት የሚውል ሎት1 ኤሌክትሮኒክስ እና ሎት 2 የኤሌክትሪክና የጥገና ዕቃዎች፣
- በየዘርፋ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የአቅራቢነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የታክስ ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት (TIN) ፤ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ ማስረጃ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ (CPO) በጨረታ የተወዳደሩበት ዕቃ በአይነት ብር 5000 /እምስት ሺህ ብር/ ብቻ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይኖርባቸዋል በካሽ እና በግል ቼክ አካውንት ማስያዝ አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ የሚያቀርቡት ኮሌጁ ለጨረታ ባዘጋጀው የሆሣዕና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ የጨረታ ሰነድ ብቻ ሲሆን ኮሌጁ ካዘጋጀው ሰነድ ውጪ የሚቀርቡ የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
- ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን ዕቃዎች የሚያቀርቡበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻው ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሆሣዕና ከተማ በሆሣዕና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ በ3ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 12 ላይ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በሆሣዕና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሣብ ቁጥር 1000021172867 ላይ ገቢ በማድረግ ደረሰኝ አቅርቦ ጨረታ መግዛት የሚቻል ሲሆን በመጨረሻው 15ኛ ቀን 11፡30 ሰዓት የጨረታ ሠነዱ ሽያጭ ያበቃና የጨረታ ሰነድ ዋናውና ኮፒ ለየብቻው በተለያዩ ፖስታዎች ታሽጎ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ በተካሄደበት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሆሣዕና ከተማ በሆሣዕና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ በ3ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 12 ላይ ለአገልግሎት በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት የሚቻል ሆኖ የጨረታ ሠነድ ማስገቢያ ሣጥን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይታሸግና በ16ኛው ቀን በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ሽያጩ በተካሄደበት ቦታ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሰዓቱ በቦታው ያለመገኘት የጨረታውን መክፈት እያስተጓጉለውም።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሆሣዕና ከተማ በሆሣዕና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ በ3ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 12 ላይ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለ90 ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የሚሰጡት የጨረታ ዋጋ ለ3 ወር ፀንቶ የሚቆይ መሆን መቻል አለበት፡፡
- 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል፡፡
- ኮሌጁ ዕቃውን ርክከብ የሚፈጽመው ኮሌጅ ግቢ ንብረት ክፍል ውስጥ ነው።
- መ/ቤቱ ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-
በስልክ ቁጥር፡- 09-13-56-82-48፤ 09-13-22-65-52 እና 09-13-10-08-89 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የሆሣዕና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ
