የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ ለእንስሳት ጤና ዘርፍ መሠረታዊ የሆኑ ግብአቶችን አግባብ ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የዲፕ ፍሪጅ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 324/17
የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ ለእንስሳት ጤና ዘርፍ መሠረታዊ የሆኑ ግብአቶችን አግባብ ካላቸው ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የዕቃው /ግዥ/ አገልግሎት ዓይነት |
ብዛት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
የሚታሸግበት ቀን |
ሰነዱ የሚገኝበት ቦታ |
|
1 |
የክትባት ማቀዝቀዣ ትልቅ ዲፕ ፍሪጅ ግዥ |
10 |
100,000 |
በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ4፡30 ይከፈታል |
ደ/ኢ/ክ/መ/ግ/ ቢሮ ዲላ መምህራን ኮሌጅ ግቢ |
በመሆኑም በንግድ ሥራ ዘርፉ የታደሰ ፈቃድ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸውና የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃዎች ያላቸውና የሚያቀርቡ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ለ60 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል፡፡
- በተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ያስያዙበትን ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በቢሮው የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11/9/2017 ዓ.ም ሎት አንድ 8፡00 ሰዓት ሎት ሁለት 9፡00 ሰዓት ሎት ሶስት 10፡00 ሰዓት ድረስ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200 በመክፈል በዲላ ከተማ መምህራን ኮሌጅ ግቢ ከሚገኘው የመ/ቤቱ የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ /ፕሮፎርማ/ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11/9/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ሎት አንድ፣ ሎት ሁለት 9፡00 ሰዓት ሎት ሶስት 10፣00 ድረስ የቴክኒካልና ፋይናንሻል የመጫራች ሰነዶችን በአንድ እናት ፖስታ በማዘጋጀት በቢሮው ግዥና/ ንብ/ አስ/ቢሮ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ሳጥን በ11/9/2017 ዓ.ም ሎት አንድ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 8፡10 ሰዓት፣ ሎት ሁለት 9፡00 ታሽጐ በዕለቱ 9፡10 ሰዓት እና ሎት ሶስት 10፡00 ታሽጎ በዕለቱ 10:10 ተጫራቾች/ ሕጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት በቢሮው የግዥና/ንብ/አስ/ቢሮ ይከፈታል፡፡
- ቢሮው በቀረበው ጨረታ ላይ አሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ስምምነት ከመፈራረሙ በፊት የግዥውን 20 ፐርሰንት መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል፡፡
- ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ 0461310134 ይጠቀሙ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ግብርና ቢሮ
