አጋርፋ የግብርና ቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ የተማሪዎች የምግብ ጥሬ እቃዎችንና የዶሮ መኖን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Agarfa Agricultural Technical Vocational Educational & Training College (አጋርፋ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ)
የዕቃ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር-01/004/2017
አጋርፋ የግብርና ቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ የሚከተሉትን ዕቃዎች: -
- ተጨማሪ የተማሪዎች የምግብ ጥሬ እቃዎችንና የዶሮ መኖን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው በመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፁትን መመሪያዎችንና ግዴታዎችን በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡ ጨረታው የሚከናወነው በግልጽ ጨረታ ሥነ-ስርዓትና ይህንኑ አስመልክቶ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሳዊ ሪፐብሊክ መንግስት በአወጣው የመንግስት ግዥ አዋጅ መሠረት ብቁ ለሆኑ አገሮች ተጫራቾች ነው።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ
- ከመስኩ ጋር አግባብነት ያለውና የአገልግሎት ጊዜው ያላለፈበት (የታደሰ የሥራ) የንግድ ሥራ ፍቃድ፤
- የግብር ክፍያ የምስክር ወረቀት /TIN/
- እንዲሁም እንደአስፈላጊነቱ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤
-
- በመንግስት ኤክትሮኒክስ ግዥ ሥርዓት (e-Government procurement system) በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
- በመንግስት የግብር ህግ መሠረት ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡና መንግስት በሚያወጣቸው ጨረታዎች ላይ መሳተፍ የሚችሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ጊዜው ያላለፈበት የድጋፍ ደብዳቤ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የሚገቡበትን ቅጽ በመሙላትና በመፈረም ከሚያቀርቡት የዕቃዎች/ለገልግሎቶች/ ዋጋ ዝርዝር ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት ዕቃ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ዋስትና /CPO/ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተጠየቀውን የጨረታ ማስከበሪያ በአጋርፋ የግብርና ቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ ሥም ማቅረብ አለበት፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለጸበት በ10 /አስር/ ቀናት ውስጥ የውል ስምምነት ካልፈፀመ ፈቃደኛ እንዳልሆነ ተቆጥሮ ለጨረታው ዋስትና ማስከበረያ ያስያዘው ገንዘብ ለኮሌጁ ገቢ ይሆናል።
- በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ሕጋዊ ተወዳዳሪዎች በአንዱ የጨረታ ሠነድ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200 /ሁለት መቶ/ ብቻ በጥሬ ገንዘብ በሕጋዊ ሠነድ በመክፈል አዲስ አበባ ኃይሌ ገ/ስላሴ ጎዳና በጌታነህ በሻህ ህንፃ በኩል ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ከአዲስ ህይወት ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው አላጌ የግብርና ቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ ጉዳይ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ከሚገኘው የአጋርፋ ኮሌጅ ጉዳይ አስፈፃሚ ጽ/ቤት እና አጋርፋ የግ/ቴ/ሙ/ት/ትና/ሥ/ኮሌጅ ግዥና ፋይናንስ ስራ አስፈፃሚ በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ይህ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ የዋጋ ማቀረቢያቸውን ኦርጅናልና ኮፒውን በመለያየት ከተያያዥ ሠነዶች ጋር በስም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ አዲስ አበባ የኮሌጁ ጉዳይ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው መክፈቻ ቀን ፡-
- ጨረታው ግንቦት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሠዓት ተዘግቶ በእለቱ ከቀኑ 8፡30 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ የኮሌጁ ጉዳይ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው መክፈቻ ቀን እንደ አጋጣሚ የህዝብ /ብሔራዊ በዓል ከሆነ የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ሰዓት እንደተጠበቀ ሆኖ በቀጣዩ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- ኮሌጁ የተሻለ ዘዴ ካአገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መሰረዝ ይችላል፡፡
ለበለጠ መረጃ፦
ስልክ ቁጥር፡-0116625004 አዲስ አበባ
0922565819/0910316003/ አገርፋ ኮሌጅ
ፋክስ ቁጥር-0221191164 አጋርፋ ኮሌጅ
ፖስታ ሣ.ቁ-15/211 ባሌ ሮቤ
አጋርፋ የግብርና ቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ
