የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
Ethiopian Electric Utility (የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት)
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ኢኤአ/ንአ/ግጨ-07/2017
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ሎት |
የሚወገደው ንብረት |
የሚገኝበት ቦታ |
መለኪያ |
ብዛት |
የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) |
የጨረታ መዝጊያ |
የጨረታ መክፈቻ |
|
1 |
ያገለገሉ እና የተለያዩ 7 ማሽነሪዎች |
ኮተቤ መካኒካል ዎርክ ሾፕ እና ጎፋ ዕቃ ግምጃ ቤት |
በቁጥር |
7 |
የመነሻ ዋጋውን 20% |
ግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት |
ግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት |
|
2 |
ያገለገሉ 8 ተሽከርካሪዎች ለመለዋወጫነት የሚያገለግሉ |
ኮተቤ ገራዥ |
በቁጥር |
8 |
የመነሻ ዋጋውን 20% |
ግንቦት 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት |
ግንቦት 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት |
ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ዝርዘር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በድርጅታችን አካውንት ቁጥር (EEU Minor Account No, 1000068699332) ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) ገቢ በማድረግ ዘወትር በስራ ስዓት ሜክሲኮ አዲስ አበባ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት በሚገኘው የንብ ባንክ ዋናው መ/ቤት 10ኛ ፎቅ ንብረት አስተዳደር ቢሮ በመምጣት የሚወገዱትን ንብረቶች ዝርዝር መረጃ የያዘ የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ ገዝተው ለአገለገሉ ተሽከርካሪዎች ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት፤ ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ለአገለገሉ ማሽነሪዎች በሳምንት ሁለት ቀን በመደበኛ የስራ ሰዓት ንብረቶቹ በሚገኙበት ኮተቤ ገራዥና ጎፋ ዕቃ ግምጃ ቤት በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Security) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን እና የጨረታ ማስከበሪያቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ስማቸውን እና ጨረታ ቁጥሩን በመግለፅ ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ድረስ ብቻ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ሜክሲኮ አዲስ አበባ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት በሚገኘው የንብ ባንክ ዋናው መ/ቤት 10ኛ ፎቅ ንብረት አስተዳደር በሚገኘው ቢሮ ይከፈታል፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-1-26-52-55/011-1-70-01-18 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ድርጅቱ የተሻል መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
