Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara National Regional State Kombolcha Directive of Finance (የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ)
  • Address Kembolcha, Ethiopia, Phone: 0913509999
  • Website
  • Deadline18 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-18 00:00:00
  • Categories Furniture , Electronics Materials

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለከተማ አስተዳደሩ መምሪያዎች አገልግሎት የሚሆን ሎት 01 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ሎት 02 ቋሚ እቃ /ፈርኒቸር/ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Amhara National Regional State Kombolcha Directive of Finance (የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ)


 

ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለከተማ አስተዳደሩ መምሪያዎች አገልግሎት የሚሆን ሎት 01 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ሎት 02 ቋሚ እቃ /ፈርኒቸር/ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ 25/08/2017 የወጣውን ጨረታ በማየት ሰነዱን መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ያላቸው፡፡
  2. የግዥ መጠኑ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ በላይ ከሆነ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  3. በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 ላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በጨረታ መክፈቻው ቀንና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ከተራ ቁጥር 1-2 ላይ የተጠቀሱትን ኦርጅናል ሰነድ ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች ከሎት 1 እስከ ሎት 2 ላሉት ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት የጠቅላላ ዋጋውን 1% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ጸንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 30 ቀናት ጸንቶ ይቆያል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 101 በመምጣት በመክፈል ለ25/08/2017 እስከ 09/09/2017 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት 11፡30 ድረስ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 114 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ከ25/08/2017 ዓ.ም እስከ 09/09/2017 ዓ.ም 11፡30 ድረስ መውሰድ ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በቀን 10/09/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልጽ ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጂ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በዓል ከሆነና የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው የመክፈቻ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  8. የጨረታው ውድድር የሚካሄደው በጥቅል ድምር ውጤት ስለሆነ የማይሞላ አይተም መኖር የለበትም፤ ያልተሞላ አይተም ከተገኘ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ይደረጋሉ፡፡
  9. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነገር ሲያጋጥማቸው ጨረታውን ካወጣው አሰሪው መስሪያ ቤት ጋር ከጨረታ መክፈቻ ከ 5 /አምስት/ ቀን በፊት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0913509999 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  10. የጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ መደረግ ይኖርበታል፡፡ ጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
  11. ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ጊዜ በኋላ ለ60 ቀናት ይሆናል፡፡
  12. ጨረታውን ለማዛባት የሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆንና ለወደፊቱም በመስሪያ ቤቱ ግዥ የማይሳተፍ እና ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወረስ ይሆናል፡፡
  13. ግዥ ፈጻሚው አካል ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በአሸናፊው ተጫራች በውድድር የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ እስከ 20% (ሃያ በመቶ) መጨመር ወይም መቀነስ የሚችል ይሆናል፡፡
  14. የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ንብረቱን ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
  15. መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ

 

Save Tender