Tender Detail

Tender Details


የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በቆሬ አካባቢ እየገነባ ለሚገኘው የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ግንባታ ፕሮጀክት (18-02B) ለፕሮጀክቱ ሰራተኞች ሰርቪስ እና ቀን እንደአስፈላጊነቱ ለፕሮጀክቱ አገልግሎት የሚሰጥ በጥሩ ይዞታ ላይ የሚገኙ ከ12 ሠው በላይ የሚይዙ ሁለት ተሽከርካሪዎችን ከነአሽከርካሪያቸው ጭምር በጨረታ አወዳድሮ ላልተወሰነ ጊዜ መከራየት ይፈልጋል፡፡


 

የተሽከርካሪ ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በቆሬ አካባቢ እየገነባ ለሚገኘው የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ግንባታ ፕሮጀክት (18-02B) ለፕሮጀክቱ ሰራተኞች ሰርቪስ እና ቀን እንደአስፈላጊነቱ ለፕሮጀክቱ አገልግሎት የሚሰጥ በጥሩ ይዞታ ላይ የሚገኙ ከ12 ሠው በላይ የሚይዙ ሁለት ተሽከርካሪዎችን ከነአሽከርካሪያቸው ጭምር በጨረታ አወዳድሮ ላልተወሰነ ጊዜ መከራየት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ባለንብረቶች ወይም ህጋዊ ውክልና ያላቸው ተወካዮቻቸው የተሽከርካሪውን ነዳጅ በተከራዩ የሚሸፈን መሆኑን በመገንዘብ በታሸገ ፖስታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜን ጨምሮ ባሉት 20 (ሃያ) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በቆሬ አደባባይ በሚገኘው የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ማዕከል የፕሮጀክት አቅርቦት እና ግዥ ቡድን ቢሮ በግንባር በመቅረብ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን በማሟላት ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  • የተሽከርካሪ ኪራይ ዋጋ በቀን
  • ተሽከርካሪው በሊትር የሚጓዝበትን ኪሎ ሜትር
  • የተሽከርካሪው ስሪት እ.ኤ.አ ከ1996 ወዲህ ቢሆን ይመረጣል፡፡
  • የተሽከርካሪዎች መነሻ (ማደሪያ) ቦታ
  • የሰርቪስ መነሻ ቦታዎች እና መስመር 1ኛ: ኮዬ ፈቼ-ቱሉ ዲምቱ-ቃሊቲ-ቆሬ አደባባይ
  • 2ኛ- መገናኛ አደባባይ -ስድስት ኪሎ-አዲሱ ገበያ 3 ቁጥር ማዞሪያ- ቆሬ አደባባይ ናቸው።

መያያዝ ያለባቸው ሠነዶች

  • የምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል፣ የግብር ከፋይ (Tin) ኮፒ የታደሰ
  • ጨረታው በ20ኛው ቀን በፕሮጀክት ቢሮ ከቀኑ በ8፡00 ሠዓት ተዘግቶ በ8፡15 ሠዓት የሚከፈት ሲሆን 20ኛው ቀን እሁድ ወይም በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
  • ከተሽከርካሪው ማደሪያ ቦታ እስከ ሰርቪስ መነሻ ቦታ ድረስ ያለው ርቀት (የነዳጅ ፍጆታ) ለተሽከርካሪው ከተሰጠው ዋጋ ጋር ተደምሮ ይሰላል፡፡
  • ድርጅቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለበለጠ መረጃ፡- ለበለጠ መረጃ 0911-89-13-78/ ወይም 011-8-72-03-83

 

በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ፕሮጀክት (18-02B)

 

Save Tender