የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ2017 በጀት አመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውል የብረታ ብረት ስራና አልሙኒየም ስራ ፣ ጣውላና ፈርኒቸር ስራ፣ የቀለም ቅብ ስራ (ፊኒሽንግ ስራ) ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ሪኤጀንት ፣ የህክምና መሳሪያ ፣ መድሃኒት ፣ የግንባታ ማቴሪያል፣ የቧንቧ እቃና ቋሚ እቃ ግዥ ለአንድ ጊዜ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ2017 በጀት አመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውል የብረታ ብረት ስራና አልሙኒየም ስራ ፣ ጣውላና ፈርኒቸር ስራ፣ የቀለም ቅብ ስራ (ፊኒሽንግ ስራ) ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ሪኤጀንት ፣ የህክምና መሳሪያ ፣ መድሃኒት ፣ የግንባታ ማቴሪያል፣ የቧንቧ እቃና ቋሚ እቃ ግዥ ለአንድ ጊዜ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም አግባብነት ያላቸውን ሁሉ በጨረታው እየጋበዝን
- ተጫራቾች ለተወዳደሩበት የአቅርቦት አይነት የተዛመደ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን-ነበር ማቅረብ የሚችሉ ፤
- የግዥው መጠን ከ200,000 በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-4 የተገለፁትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታው ኦሪጅናል ሰነዶች ጋር ማቅረብ ይጠበቃል።
- ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የስራ ቀናት ከሆስፒታሉ ግዥ ክፍል የማይመለስ 200 ብር በመክፈል ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% ሲፒኦ ከአሪጅናሉ የጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፓስታ ሙሉ ስምና አድራሻ ጽፎ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም ኦርጅናል ሰነዱ እና ፎቶ ኮፒ ለብቻው ሙሉ አድራሻው ተጽፎ በጥንቃቄ ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
- የጨረታው ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በማስታወቂያ በወጣበት በመጨረሻ 16ኛው ተከታታይ ቀን በ4፡00 ታሽጎ በእለቱ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ሆስፒታሉ ቫት እና ዊዝ ሆልድ (2%) ቆርጦ የሚያስቀር መሆኑን እንገልፃለን ፡፡
የደሴ አጠ/ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
