Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የቃሊቲ ትራኪንግ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ቺፍ ኦፕሬሽን ቃሊቲ ትራኪንግ የቀድሞ ስም፦ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ የብስ ትራንስፖርት ቃሊቲ ቅርንጫፍ በተለምዶ ቃሊቲ ጉምሩክ ጊቢ ውስጥ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114-40-40-78
  • Websitehttps://www.eslse.et/
  • Deadline17 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-17 00:00:00
  • Categories Food And Beverage , Food Items And Drinks

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ቃሊቲ ትራኪንግ ቅ/ጽ/ቤት ዘወትር ሥራ ቀን ለሠራተኞች የሚቀርብ በቀን ከ69 እስከ 80 ሊትር የሚሆን የታሸገ ፓስቸራይዝድ ወተት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ውል መግዛት ይፈልጋል፡፡

በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የቃሊቲ ትራኪንግ ቅ/ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ቃሊቲ ትራኪንግ ቅ/ጽ/ቤት ዘወትር ሥራ ቀን ለሠራተኞች የሚቀርብ በቀን ከ69 እስከ 80 ሊትር የሚሆን የታሸገ ፓስቸራይዝድ ወተት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ውል መግዛት ይፈልጋል፡፡

የጨረታ መለያ ቁጥር ፡- ESL/KT/NCB/M/O19/17

ተ.ቁ

የምርት አይነት

መለኪያ

በቀን የሚፈለገው የወተት መጠን

1

የታሸገ ፓስቸራይዝድ ወተት

በሊትር

ከ69-80

 

ስለሆነም፡-

  1. ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸውና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፣
  2. ተጫራቾች ከኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው፣
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ወተት በ500 ሚሊ ሊትር የታሸገ መሆን አለበት፣
  4. ተጫራቾች ለተወዳደሩበት የወተት አቅርቦት ዋጋ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) 20,000.00 (ሃያ ሺ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ብቻ Ethiopian Shipping & Logistics Service Enterprise Kality Branch Office በሚል በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ቃሊቲ በሚገኘው በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ቃሊቲ ትራኪንግ ግዥ ዋና ክፍል ቢሮ ቁጥር 108 ቀርበው የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በድርጅቱ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000008631925 (Ethiopian Shipping & Logistics Service Enterprise Kality Branch Office) ገቢ በማድረግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ኦርጂናል እና ኮፒ “Posta” ላይ የጨረታ መለያ ቁጥር በመፃፍ በቅ/ጽ/ቤቱ የግዥ ዋና ክፍል ቢሮ ቁጥር 108 እስከ ጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  7. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር በ16ኛው ቀን 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
  8. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0114-40-40–78 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

 

በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የቃሊቲ ትራኪንግ ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender