Tender Detail

Tender Details


በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ አላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2017 በጀት ዓመት መድኃኒት፣ የላቦራቶሪ ሪኤጀንቶችንና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን ግዥ ለመፈጸም እንዲቻል በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው አቅራቢዎች መካከል አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ የአላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ አላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2017 በጀት ዓመት መድኃኒት፣ የላቦራቶሪ ሪኤጀንቶችንና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን ግዥ ለመፈጸም እንዲቻል በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው አቅራቢዎች መካከል አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ሎት-1 የመድኃኒት ግዥ፣

ሎት-2 የላቦራቶሪ ሪኤጀንቶች፣

ሎት-3 የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች

በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች መወዳደር ይችላሉ።

  1. በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  2. ተጫራቾች ለእያንዳንዳቸው ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
  3. የጨረታ ሰነዱን ከአላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 110 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት በመጠቀም ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
  4. የጨረታ ሰነዱን በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጅናልና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም በአላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 110 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት በ4፡30 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 110 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት፣ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ ዘግይቶ የሚደርስ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ ተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 046-2-12-95-60

 

በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ የአላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

 

Save Tender