Tender Detail

Tender Details

  • Company የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ
  • Address ቤሬ ቀበሌ አዲስ ከሚሰራው ሪፈራል ሆስፒታል ፊት ለፊት ፡ አርባ ምንጭ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 046-181-05-00
  • Website
  • Deadline16 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-17 00:00:00
  • Categories Pumps, Motors And Compressors

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የውሃ መሳቢያ ፓምፕ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ


 

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የውሃ መሳቢያ ፓምፕ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል። ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች፣

  1. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፡፡
  3. በፋይናንስ መስሪያ ቤቶች ዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ ማንኛውም ተጫራች መሳተፍ ይችላል፡፡
  4. ለእያንዳንዱ የተዘጋጀ ጨረታ ዓይነት ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከመ/ቤቱ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል መግዛት ይችላል፡፡
  5. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ የቴክኒካል የጨረታ ሰነድና የፋይናንሻል የጨረታ ሰነድን ለብቻ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለእያንዳንዱ ተመሳሳይ አንድ አንድ ኮፒዎች አዘጋጅተው በየኤንቨሎፑ የውጭ ገጽ ዋና /ኦርጅናል/ ወይም ኮፒ ብሎ በመጻፍና አሽገው ለዚህ አገልግሎት በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን የሚያስገቡበት የመጨረሻ ቀን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ሲሆን በ15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት በፊት ብቻ ይሆናል፡፡ ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በሚቀጥለው ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በግልጽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም 16ኛ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይሆናል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለውሃ መሳቢያ ፓምፕ 80,000 (ሰማንያ ሺህ ብር) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ CPO ቼክ፤ ባንክ ጋራንቲ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች ጨረታ በሚከፈትበት ቀን ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
  9. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ/ጉ/አቅራቢ/ዎች/ተጨማሪ መረጃ የሚፈልጉ ከሆነ በስልክ ቁጥር 046-181-05-00 ዘወትር በስራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ:

መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የመ/ቤቱ አድራሻ፡- ቤሬ ቀበሌ አዲስ ከሚሰራው ሪፈራል ሆስፒታል ፊት ለፊት የደቡብ ኢትዮጵያ

ክልል የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ

አ/ምንጭ

 

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የሥራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ

 

Save Tender