የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ አስተዳደር ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የአገልግሎት ግዥ ለ2017 በጀት ዓመት አወዳድሮ አገልግሎት ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ አስተዳደር
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 04/2017
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ አስተዳደር ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የአገልግሎት ግዥ ለ2017 በጀት ዓመት አወዳድሮ አገልግሎት ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
ሎት 1. የመኪና ጥገና
ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋበዛሉ፡፡ በዚህም መሰረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አግባብነት ያለው የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈለ የቫት ተመዝጋቢዎች የሆኑ
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን በመገኘት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚጫረቱበት የጨረታ ሎት ዓይነት መኪና ጥገና 50,000 (ሃምሳ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ሰነድ የስራውን ዝርዝር የሚገልጽ ቴከኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ ለየብቻ ዋናውን (ኦርጅናል) እና የማይከፈት ኮፒ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ስምና አድራሻ በመጥቀስ የድርጅቱ ማህተም ያረፈበትን ፖስታ ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ ለዚህ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን 4፡30 ላይ ይከፈታል የጨረታው መክፈቻ ቀን በዓል ከሆነ በማግስቱ ባለው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የነጠላ ዋጋ በሰነዱ ላይ በመግለጽ ሙሉ አድራሻና ማህተም መጠቀም አለባቸው፡፡
- የተሻለ አማራጭ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- ሙሉ ኦርጅናል የሚገዙትን የጨረታ ሰነድ ዋጋ ተሞልቶበት ህጋዊ ማህተም እና በየገፁ ፊርማ ተደርጐበት መመለስ አለበት ካልተመለሰ ከጨረታ የሚሰረዝ መሆኑን እንገልጻለን፣
አድራሻ፡- ቤተል ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አጠገብ ያለው ህንጻ ላይ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አሰተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ፑል የአስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02
ስልክ ቁጥር፡- 0118 34-09-79
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ አስተዳደር
