Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን የእምድብር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ጉራጌ ዞን የእምድብር ከተማ ፡ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0921542357
  • Website
  • Deadline12 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-12 00:00:00
  • Categories Chemicals And Reagents , Health Care, Medical Industry Materials And Machinery

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን የእምድብር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለእምድብር ከተማ ጤና ጣቢያ ለእናቶችና ህጻናት አገልግሎት የሚውል የህክምና መገልገያ አልትራሳውንድ /Ultrasound/ እና የሚያስፈልገው ሬጀንቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን የእምድብር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

መለያ ቁጥር 004/2017

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን የእምድብር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለእምድብር ከተማ ጤና ጣቢያ ለእናቶችና ህጻናት አገልግሎት የሚውል የህክምና መገልገያ አልትራሳውንድ /Ultrasound/ እና የሚያስፈልገው ሬጀንቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም

  1. በንግድ ዘርፉ የተሰማራቹህ ተወዳዳሪዎች የዘመኑ ግብር የከፈላቹህ ህጋዊ የታደሰ የስራ ፍቃድ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ ቲን ነምበር እና የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላችሁ፡፡
  2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታው ሰነድ በማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ የእምድብር ከተማ አሰተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት በመክፈል ሰነዱን በእምድብር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዢ ክፍል በመምጣት መግዛት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንታችሁ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በማድረግ ከላይ በተራ ቁጥር 1 ላይ የተዘረዘሩ ማስረጃዎች 1 ኦርጅናል ሰነድና 2 ኮፒ በተለያዩ በታሸጉ ፖስታች በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባችሁ፡፡
  4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ /10/ አስር/ የስራ ቀናቶች አየር ላይ ይውላል እስከዛ ድረስ የጨረታ ዶክመታችሁ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ ጨረታው የሚያበቃው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 /ስምንት ሰዓት/ ላይ የጨረታው ሳጥን ታሽጎ የዛኑ ቀን ከቀኑ 8፡30 /ስምንት ሰዓት ተኩል/ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ጨረታው ለመክፈት የሚያግድ ነገር የሌለ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  5. የሚከፈትበት ቀን በዓል /ቅዳሜና እሁድ/ ከሆነ ለሚቀጥለው የስራ ቀን ይተላለፋል፡፡
  6. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም ቢድ ቦንድ /bid bond/ 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በእምድብር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም አሰርተው ከጨረታው ሰነድ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡- ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ /bid bond/ የምታቀርቡ ከሆነ 60 /ስልሳ/ ቀንና ከዚያ በላይ የሚቆይ መሆን አለበት፡፡

 

ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ 0921542357/0926928268

 

በጉራጌ ዞን የእምድብር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender