በየካ ክፍለ ከተማ ኮተቤ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች በዝርዝር የተጠቀሱትን ነገሮች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በየካ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የኮተቤ ጤና ጣቢያ
የ2ኛ ዙር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 002/2017
በየካ ክፍለ ከተማ ኮተቤ ጤና ጣቢያ
ሎት 1 የደንብ ልብስ የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ብር 4000 (አራት ሺህ ብር)
ሎት 2 የጽዳት እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 3000 (ሶስት ሺህ ብር)
ሎት 3 የጽህፈት መሣሪያዎች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 3000 (ሶስት ሺህ ብር)
ሎት 4 የኤሌክትሪክ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 2000 (ሁለት ሺህ ብር)
ሎት 5 ሕትመቶች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 3000 (ሶስት ሺህ ብር)
ሎት 6 የጥገና እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 4000 (አራት ሺህ ብር)
ሎት 7 የቧንቧ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 2000 (ሁለት ሺህ ብር)
ሎት 8 መድኃኒቶች እና የህክምና መሳሪያዎች ጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 5000 (አምስት ሺህ ብር)
ሎት 9 ሪኤጄንቶች የጨረታ ማስከበሪያ ብር ሲፒኦ 3000 (ሶስት ሺህ ብር) አወዳድሮ ማግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡፡
- ሕጋዊ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ ማስገባት ይኖርበታል።
- የግብር መክፈያ ግዴታዎችን የተወጡ መሆኑን የሚገልፅ ከግብር አስገቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
- ጨረታው በሚወዳደሩበት በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ መሆን አለበት።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር በየሎት ላይ በተዘረዘረው መሰረት ማስያዝ ይኖርበታል፡ የጨረታ ሰነዱን ሲያስገባ (በC.P.O) ብቻ በጤና ጣቢያ ስም አሰርቶ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ (በC.P.O) ያስያዙት ብር ለተሸነፉ ድርጅቶች ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል፡፡
- ጨረታውን ለአሸነፉ ድርጅቶች ደግሞ የጨረታውን ውል ማስከበሪያ ብር 10% አስይዘው እንደተፈራረሙ ለጨረታ ማስያዣ የተያዘው ብር ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘውን ሰነድ በየሎቱ በማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 (አስር የስር ቀናት ውስጥ) ዘወትር በሥራ ሰዓት ኮተቤ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 55 ግዥ ክፍል በአካል ቀርቦ የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ አድራሻ፣ ፊርማ እና የድርጅታቸውን ማህተም ማድረግ አለባቸው።
- ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ መሰረት ማድረግ የሚጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት አንድ ኮፒ እና ኦርጅናል አሽገው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በጤና ጣቢያው 4ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 54 በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት በአስራ አንደኛው ቀን በ3፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ (ሶስት ሰዓት ተኩል) ላይ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጤና ጣቢያው የሚገዛቸውን እቃዎች 20% የመጨመር እና የመቀነስ መብት አለው፡፡
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከሚከፈትበት ዕለት ጀምሮ 60 ቀናት እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 28 ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር- 0911052054 / 0921830596 እና 011164622973 ደውለው ይጠይቁ
አድራሻ፡- ኮተቤ ጤና ጣቢያ 02 ወደታች በሚወስደው መንገድ 600 ሜትር ገባ ብሎ ነው::
በየካ ክፍለ ከተማ የኮተቤ ጤና ጣቢያ
