በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ሥር የሚገኘው ሁለ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት ለሥልጣና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Sidama National Regional Sate Job, Skill And Enterprises Development Bureau (ሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ)
የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ሥር የሚገኘው ሁለ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት ለሥልጣና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ማለትም
1. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ዝርዝር
- ላፕቶፖች
- ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች
- ፕሪንተሮች
- ፍላሾች
- ሌሎች ቁሳቁሶችን ያካትታል ፡፡
በዚሁ መሠረት
- ተጫራቾቹ የዘመኑን ግብር በመገበር በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤
- ተጫራቾቹ የVAT ተመዝጋቢ የሆኑ፤
- ተጫራቾቹ የጨረታ ማስከበሪያ (BID security) CPO በሁላ ኮ/ኢ/ኮሌጅ ስም በማሰራት ከሚያቀርበው ዋጋ የባንክ 10% ማቅረብ የሚችሉ፣
- የመወዳደሪያ ሠነዱን 200 ብር (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከሁላ ኮ/ኢ/ኮሌጅ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾቹ የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚችሉት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይሆናል፣
- ተጫራቾቹ የጨረታ ሰነዶችን በኦርጅናልና በኮፒ ተደርጎ በማሸግ በሁለት ፖስታዎች ላይ የድርጅቱን አድራሻ የሚገልጽ ህጋዊ ማህተም ስምና ፊርማ በማኖር በተለያዩ ፖስታዎች የታሸጉትን ኦርጅናልና ኮፒ ሁለቱንም ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ በማስገባት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ይከፈታል፣
- ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
- ጨረታ አሸናፊው ግለሰብ ወይም ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎችን በራሱ ትራንስፖርት እስከ ኮሌጁ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- 09 16 30 76 49/09 26 58 63 41
ሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ
