የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የተቋሙ ሰራተኞች ወደ ቢሮ ሲመጡና ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲመለሱ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎችን ለመከራየት አቅዷል፡፡ በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች የጨረታ ማስከበሪያ 10,000.00 /አስር ሺህ/ ማስያዝ የሚችሉ በመንግስት ግዥ ጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
National Rehabilitation Commission (ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን)
የተሽከርካሪ ኪራይ የአገልግሎት ግዥ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ብ/ተ/ኮ/018/2017
የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የተቋሙ ሰራተኞች ወደ ቢሮ ሲመጡና ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲመለሱ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎችን ለመከራየት አቅዷል፡፡ በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች የጨረታ ማስከበሪያ 10,000.00 /አስር ሺህ/ ማስያዝ የሚችሉ በመንግስት ግዥ ጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የተሰማሩና የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፤
- በዘርፉ የተሰማሩ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ሰርተፊኬት ያላቸው፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ያላቸው፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና በጨረታ መሳተፍ እንዲችሉ ክሊራንስ ያላቸው፤
- በመንግስት ግዥ በአዲሱ የኤሌክትሮኒክስ ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡ፤
ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ አስራ አምስት /15/ ቀናት ውስጥ አድራሻ በእንግሊዝ ኤምባሲ ፊት ለፊት ወደ ባልደራስ በሚወስደው መንገድ 500 ሜትር ወደ ቀኝ ገባ ብሎ በሚገኘው የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ህንፃ 2ኛ ፎቅ ግዥና ፋይናንስ ስራ አስፈፃሚ በአካል በመቅረብ የማይመለስ /500/ አምስት መቶ ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል፡፡ ተጫራቾች ፋይናንሻል እና የቴክኒከ ሰነድ ለየብቻ በማሸግ አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ ሰነድ በተገለፀው መሰረት እስከ /16/ አስራ ስድስተኛው ቀን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በአስራ ስድስተኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ይከፈታል፡፡
ተቋሙ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን
