የካፋ ማህበረሰብ ቴሌቭዥን ጣቢያ በ2017 በጀት ዓመት ለቴሌቭዥን ጣቢያ አገልግሎት የሚውሉ የድሮን ካሜራ እና የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልዕ ጨረታ ማስታወቂያ ተጫራቾችን በመጋበዝ ለመግዛት በሎት እንደሚከተለው አስከ በጀት ዓመቱ ማብቂያ ማለትም እስከ ሰኔ 30/2017 ዓ/ም ድረስ አቅርቦዋል፡፡
Kafa Zone TV (የካፋ ማህበረሰብ ቴሌቭዥን ጣቢያ)
የጨረታ ማስታወቂያ
ግ/ጨ/ቁጥር 01/2017
የካፋ ማህበረሰብ ቴሌቭዥን ጣቢያ በ2017 በጀት ዓመት ለቴሌቭዥን ጣቢያ አገልግሎት የሚውሉ የድሮን ካሜራ እና የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልዕ ጨረታ ማስታወቂያ ተጫራቾችን በመጋበዝ ለመግዛት በሎት እንደሚከተለው አስከ በጀት ዓመቱ ማብቂያ ማለትም እስከ ሰኔ 30/2017 ዓ/ም ድረስ አቅርቦዋል፡፡
ሎት1. የድሮን ካሜራ
ሎት2. የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ፤ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ፤ የቲን /TIN/ እና ቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች የጨረታ ዶክመንት ሊገዙ ሲመጡ ኦሪጂናሉን እና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ አቅርበው እንዲመሳከር የማድረግ ግዴታ አለባቸው።
በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብር/ የካፋ ማህበረሰብ ቴሌቭዥን ጣቢያ በተከፈተው ሒሳብ ቁጥር 1000501606379 በማስገባት የባንክ ስሊፕ በመያዝ የካፋ ማሀበረሰብ ቴሌቭዥን ጣቢያ ሕንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ አ
- የድሮን ካሜራ ብር 100,000.00/መቶ ሺህ ብር/
- የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ብር 50,000.00 /ሀምሳ ሺህ ብር/ በካፋ ማህበረሰብ ቴሌቭዥን ጣቢያ ግዥ ንብ/አስ/ሥም በማሰራት ከኦሪጅናልና ቴክኒካል የጨረታው ዶክመንት ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጊዜ ሰነዱ ላይ ዋጋ በመፃፍ በሰም /በሙጫ/ በታሸገ ኤንቨሎፕ ፋይናንሻልና እና ቴክኒካል የጨረታ ዶክመንት ተገቢውን ፈርማ እና ማህተም በማሳረፍ ለየብቻ አንዳንድ ኦሪጂናል የተሟላ ሰነድ በሰም /በሙጫ/ በታሸጉ ፖስታዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በካፋ ማህበረሰብ ቴሌቭዥን ጣቢያ ግዥ ንብ/አስ/በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ሳጥን በ16ኛው ቀን በ3፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በካፋ ማህበረሰብ ቴሌቭዥን ጣቢያ ይከፈታል፡፡ የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ በመክፈቻው ዕለት የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች ያለመገኘት የጨረታ መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
- ተጫራቾች አሰሪው መ/ቤት ያዘጋጀውን የቴክኒካል ዶክመንት መጠይቅ ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ማሸነፉ ሲረጋገጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ለማስያዝ ፈቃደኛ መሆን አለበት፡፡
- አሸነናፊው ማሸነፉ ከተገለፀበት ጀምሮ 7 /ሰባት/ የሥራ ቀናት በኋላ በቴሌቭዥን ጣቢያው በመገኘት ውል መግባት አለበት፡፡
- ቴሌቭዥን ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በሞባይል ቁጥር- 0925 26 39 13/0924 81 30 22 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የካፋ ማህበረሰብ ቴሌቭዥን ጣቢያ
ቦንጋ
