Tender Detail

Tender Details

  • Company በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የቢሾፍቱ ሞተር ቬይክልስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ
  • Address ቢሾፍቱ /ደብረዘይት ከተማ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0994521556
  • Website
  • Deadline05 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-05 00:00:00
  • Categories Labour Outsourcing Services

በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የቢሾፍቱ ሞተር ቬይክልስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ የተቋሙን ዋናውን የበር መግቢያ (Main Gate) እና አካባቢውን የማስዋብ ስራ ለማሰራት በስራ ዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የቢሾፍቱ ሞተር ቬይክልስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ


 

የግልፅ ጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ

ቁጥር ቢሞቬኢኢ/ግጨሰ/ 04/2017

 

በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የቢሾፍቱ ሞተር ቬይክልስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ የተቋሙን ዋናውን የበር መግቢያ (Main Gate) እና አካባቢውን የማስዋብ ስራ ለማሰራት በስራ ዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

  • ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
  1. ማንኛውም ተጫራች አግባብነት ያለው በ2017 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የወቅቱን ግብር የከፈሉ መሆን አለበት፡፡
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ (VAT) የተመዘገቡና (Tin No.) ያላቸው መሆን አለበት፡፡
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በማያሻማ ሁኔታ መግለፅና ሙሉ አድራሻቸውን መጥቀስ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከዋናው ሰነድ ጋር በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ መሰረት በጥራትና በተቀመጠው ስፔስፊኬሽን መሠረት ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች በሎቱ ለቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር በዘርፉ ስራ ወይም ንግድ ላይ ስለመሰማራታቸው ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ከዚህ ውጪ ተወዳድረው ቢገኙ ያስገቡት መወዳደሪያና ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የመጫረቻውን ጠቅላላ ዋጋ 2% (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤ 2% (CPO) ያላስያዘ ተጫራች ከጨረታው ውጪ ይደረጋል፡፡
  7. በጨረታው ተሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች 2% የጨረታ ማስከበርያ (CPO) ዋስትና የጨረታ አሸናፊው እንደታወቀ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
  8. የጨረታውን አካሄድ ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ ይሆናሉ፤ ለወደፊትም በኢንዱስትሪው ጨረታ አይሳተፉም ያስያዙትም የጨረታ ማስከበሪያ ይወረሳል፡፡
  9. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራች ከኢንዱስትሪው ጋር የሥራ አፈፃፀም ውል መፈራረም አለበት ውል ካልፈረመ የስያዘው 2% (CPO) ተወርሶ ለኢንዱስትሪው ገቢ ይደረጋል ፡፡
  10. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በግልፅ በኢትዮጵያ ብር ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ በዝርዝር መስፈር አለባቸው፡፡ በዋጋው ላይ ማንኛውም ታክስና ተጨማሪ እሴት ታክስ ያካተተ መሆኑና አለመሆኑ መገለፅ አለበት፡፡
  11. በነጠላ ዋጋና በጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ቢኖር ነጠላ ዋጋ ተቀባይነት እንዲኖረው ተደርጎ በነጠላ ዋጋው ተመስርቶ ጠቅላላ ዋጋው ይታረማል፡፡
  12. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በኢንዱስትሪው ቅጥር ግቢ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ የጨረታ ሳጥኑ ከሚዘጋበት ሰዓት በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

 

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ

 

Save Tender