Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን የላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለላስታ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል፡- ሎት 01 የጽ/መሣሪያ፣ ሎት 02 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 03 የውሃ የኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች/ ሎት 04 የግንባታ እቃዎች /ኮንስትራክሽን እቃዎች/ በመደበኛ በጀትና በተራድኦ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር የላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን የላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለላስታ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል፡- ሎት 01 የጽ/መሣሪያ፣ ሎት 02 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 03 የውሃ የኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች/ ሎት 04 የግንባታ እቃዎች /ኮንስትራክሽን እቃዎች/ በመደበኛ በጀትና በተራድኦ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።

  1. በአዲሱ የንግድ አዋጅ መሠረት የእያንዳንዱ ሎት የተናጠል በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ሰርተፊኬት ያላቸውና የሚሞሉት ዋጋ ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው።
  2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ የኢት ብር 65.00 /ስልሳ አምስት ብር/ በመክፈል ላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለሎት 03 የውሃ ኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች 37,500 /ሰላሳ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር/ እና ሌሎቹ ሎቶች 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ለየብቻ ለተጠየቁት ሎቶች ለጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ከፖስታው ውስጥ አብሮ መግባት ወይም ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን አንስቶ የሚቆጠር 15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ሎት 01 የጽሕፈት መሣሪያ፣ ሎት 02 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 03 የውሃ የኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች፣ ሎት 04 የግንባታ እቃዎች /ኮንስትራክሽን እቃዎች/ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  5. የተጠቀሰው ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም በካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይተላለፍና ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ኮፒና አሪጅናል በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  7. አሸናፊው አካል ዕቃዎችን በራሱ ትራንስፖርት ላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አጓጉዞ ማቅረብ ይኖርበታል።
  8. የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
  9. ተጫራቾች በአንድ ሎት ውስጥ የተዘረዘሩትን የዕቃ አይነቶች ከፋፍሎ መሙላት አይቻልም ውድድሩ በየሎት ምድቡ ጥቅል ብር ወይም ድምር ስለሆነ የሁሉም ዋጋዎች መሞላት አለበት።
  10.  መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
  11.  ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ወይም ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል በመቅረብ ወይም ከዚህ በታች በተጠቀሱት ስልክ ቁጥሮች 033-3-36-01-249 ወይም 09-13-66-97-14 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

የላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender