በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀዲያ ዞን ሾኔ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለሾኔ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ለአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት አገልግሎት ማዘመን በሚል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ እስካነር እና ለኔት ወርክ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
የሾኔ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀዲያ ዞን ሾኔ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለሾኔ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ለአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት አገልግሎት ማዘመን በሚል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ እስካነር እና ለኔት ወርክ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ግዥውን የሚፈዕመው በጥራትም ሆነ በዋጋ ብቁ መሆናቸውን አረጋግጦ ከመረጣቸው ይሆናል፡፡
- የተፈላጊ ዕቃ ዝርዝር በዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ ይገኛል፡፡
- የመወዳደሪያ ሀሳቦቹ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ ሆነው ለግዥ ፈፃሚ መ/ቤት ሾኔ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ር ቢሮ ቁጥር 10 መድረስ አለበት፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከሾኔ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ሥራ ሂደት ቢሮ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታውን ሰነድ ቴክኒካልና ፋይናሻል ዋናውና ኮፒውን በተለያየ አሽጎ በአካል ወይም በሕጋዊ ወኪል ቀርቦ መወዳደር የሚችል መሆኑን እየገለጽን የጨረታው ሣጥን በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሠዓት ታሽጎ በዕለቱ 9፡00 ሠዓት ይከፈታል። የሚታሸግበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን የመንግሥት ሥራ ግብር የከፈሉ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር VAT ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው፡፡
- የዕቃዎች ማስረከቢያ ቦታ ሾኔ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ር መጋዘን ነው፡፡ ማስረከቢያ ጊዜው ተጫራች ውል ከገባበት ጊዜ ጀምሮ በሚሰጥ ቀናት ውስጥ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 18,000.00 /አስራ ስምንት ሺህ ብር ብቻ/ በ CPO ወይንም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው:: የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ጊዜ አንስቶ ለ 60 ቀናት ይሆናል፡፡
- አቅራቢዎች በእያንዳንዱ የዕቃ ዝርዝር ማቅረቢያ ሠንጠረዥ ውስጥ የዕቃውን ዓይነትና ነጠላ ዋጋ በመሙላት እንዲሁም ቀን ፈርማ የድርጅቱን ማህተም ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የዕቃው ነጠላ ዋጋ ታክስን የሚያካትትና የማያካትት መሆኑ በትክክል መገለጽ አለበት፡፡ ታክስ በትክክል ካልተገለፀ የቀረበው ዋጋ ታክስን እንዳካተተ ተቆጥሮ ውድድሩ ይካሄዳል፡፡
- ዕቃዎቹ ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች ተያይዘዋል፡፡
- አሸናፊው አቅራቢ የሚለየው ለእያንዳንዱ ዕቃ በቀረበው ዝቅተኛ ዋጋ ይሆናል፡፡ በዚህ መሠረት ለሁሉም ዕቃዎች ዝርዝር ዋጋ ያላቀረበ ተጫራች ከውድድሩ ወጪ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን ማስገባት ይኖርበታል። ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በኋላ የቀረበ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ተቀባይነት የሌለው ሲሆን ኤንቨሎፑ ሳይከፈት ለተጫራች ተመላሽ እንዲሆን ይደረጋል፡፡
- ጨረታው የቴክኒከ መስፈርቱን ካሟሉት አቅራቢዎች መካከል ዝቅተኛ ዋጋ ላቀረበው ተጫራች አሸናፊ ይደረጋል፡፡
ከሚከተሉት ጥፋቶች አንዱን የፈጸመ ከውድድር ውጪ ሊደረግ ይችላል፡፡
- ቀደም ሲል በወጡ ውድድሮች የገባውን ግዴታ ሳያከብር የቀረ ከሆነ፣
- ውድድሩን ለማሸነፍ ለማንኛውም ኃላፊ ወይም ባለሙያ የመደለያ ሃሳብ መስጠቱ ሲረጋገጥ፣
- በግዥ ኤጀንሲ በኩል እገዳ የተጣለበት ከሆነ፣
ማሳሰቢያ፡- ለመ/ቤቱ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ውድድሩን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ 09-10-80-60-12/09-11-91-80-05 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሾኔ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
