ኦሮሚያ ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ ዕቃዎች በጨረታ በማወዳደር ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ መሸጥ ይፈልጋል::
Oromia Bank S.C (ኦሮሚያ ባንክ አ.ማ)
Oromia Bank
Oromia Bank Baankii Oromiyaa
የጨረታ ቁጥር: ግፋዳ/አፋማ/004/2017
ያገለገሉ ዕቃዎች የጨረታ ሽያጭ
ማስታወቂያ ቁጥር 004/2017
ኦሮሚያ ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ ዕቃዎች በጨረታ በማወዳደር ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ መሸጥ ይፈልጋል:: ስለዚህ ዕቃዎቹን መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የማይመለስ ብር 150.00 (አንድ መቶ አምሳ) በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ቦሌ መንገድ ጌቱ ኮሜርሽያል ሴንተር ህንፃ ጎን ከሚገኘዉ የባንኩ ዋና መ/ቤት 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 407-8-1 (አሴት እና ፋሲሊቲ ማኔጅመንት ዋና ክፍል) በመውሰድ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላል::
- ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ ዕቃዎች አቃቂ ዩኒሳ አደባባይ አካባቢ (ከአንበሳ ቆርቆሮ ፋብሪካ ጎን) ከሚገኘው የባንኩ መጋዘን በአካል ተገኝተው በማየት ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ እስከ ሚያዝያ 29 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተገለፀዉ የባንኩ ዋና መ/ቤት አድራሻ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ::
- ጨረታዉ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 8፡00 ላይ ተዘግቶ 8፡30 ሰዓት ላይ በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት መገኘት በሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት ይከፈታል::
- ተጫራቾች ለጀነሬተር ጨረታ ማስከበሪያ የብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) ሲ.ፒ.ኦ እንዲሁም ለሌሎች ዕቃዎች የብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ) በኦሮሚያ ባንክ አ.ማ. ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
|
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
ብዛት |
|
1 |
የተለያዬ ኬቪኤ መጠን ያላቸዉ ያገለገሉ ጄነሬተሮች (ፔርኪንስ-ኢንጂን) |
2 |
|
2 |
የተለያየ መጠን ያላቸዉ ያገለገሉ የቡናና የፎቶኮፒ ማስቀመጫ ጠረጴዛዎች |
8 |
|
3 |
የተለያየ ዓይነት ያገለገሉ ባለ አንድ እና ባለ ሶስት የደንበኛ መቀመጫ ወንበሮች |
86 |
|
4 |
የተለያየ ዓይነት ያገለገሉ ባለመደገፊያ ተሽከርካሪ ወንበሮች |
90 |
|
5 |
ከባንኩ ቅርንጫፎች የተነቀሉ የተለያዬ መጠን ያለቸዉ ያገለገሉ የቅ/ፍ ስም ማስታወቂያ ሰሌዳዎች |
11 |
|
6 |
የተለያየ ዓይነት ያገለገሉ የገንዘብ መቁጠሪያ እና መለያ ማሺኖች |
72 |
|
7 |
የተለያየ ዓይነት ያገለገሉ የዴስክ ቶፕ እና ላፕቶፕ ኮምፒዩተሮች |
42 |
|
8 |
የተለያየ ዓይነት ያገለገሉ የዴስክ ቶፕ ኮምፒዩተር ሞኒተሮች (Screen) |
84 |
|
9 |
የተለያየ ዓይነት ያገለገሉ እስካነሮች እና ፕሪንተሮች |
23 |
|
10 |
የተለያየ ዓይነት ያገለገሉ የፎቶ ኮፒና የፋክስ ማሽኖች |
21 |
|
11 |
ያገለገሉ የኤሌክትሪክ የሂሳብ ማሽኖች |
24 |
|
12 |
የተለያየ ዓይነት ያገለገሉ የገንዘብ ማስቀመጫ ካዝናዎች |
5 |
|
13 |
የተለያየ መጠን ያላቸዉ ያገለገሉ የጥበቃና የጄኔሬተር ቤት/መጠለያ |
25 |
|
14 |
የተለያዩ ያገለገሉ ባለ አራት ኪስ ካዎንተር መሳቢያዎች |
4 |
|
15 |
የአየር ማቀዝቀዣ/Air conditioner/ |
4 |
|
16 |
ያገለገሉ የመተያቢያ ማሽኖች (Type Writer Machines) |
6 |
|
17 |
ያገለገሉ ባለ አራት መሳቢያና ላተራል የፋይል ማስቀመጫ ካቢኔቶች |
11 |
|
18 |
ከብረት የተሰሩ ያገለገሉ የገንዘብ ማስቀመጫ ሳጥኖች |
15 |
|
19 |
ከባንኩ ቅርንጫፎች የተነቀሉና የተለያየ መጠን ያለቸው ያገለገሉ ካዎንተሮች |
ባለበት |
ኦሮሚያ ባንክ አ.ማ
መደበኛ ስልክ ቁጥር:- 0115-57-20-37/95 ተንቀሳቃሽ
ስልክ ቁጥር፡- 0912-73-64-32/0913-46-99-87/0911-69-53-48
